አንድን ነገር ለማድረግ ስሜታችን ሲነሳሳ ስሜቱን ለመግራት መለማመድ ከሚገቡን አስፈላጊ ልምምዶች አንዱ ለስሜቱ ምላሽ ሰጥተን ብናደርገው የሚያስከትለውን ውጤት በሚገባ ማጤን ነው፡፡
በእርግጥ ነው ስሜት እንዲጦዝ ስንፈቅድለት፣ በስሜቱ አቅጣጫ ወደ ተግባር ለመግባት “የውሸት ምክንያትን” ከዚህም ከዚያም ብለን የማምጣት ዝንቤሌ ሊኖረን ይችላል፡፡ የውሸት ምክንያት ብለን የምንጠራው አይነት ምክንያት ሰዎች ያደረጉብንን ነገር እንደ ሰበብ መቁጠር፣ “ተጎድቻለሁ” የሚል ሰበብ መስጠትና የመሳሰሉት ምክንያቶችን ጠቋሚ ነው፡፡
ለወደፊቱ፣ አንድ ተገቢ ያልሆነ ስሜት ሲሰማችሁ ምንም አይነት እርምጃ ከመውሰዳችሁ በፊት ለስሜቱ ምላሽ መስጠት የሚያስከትለውን ውጤት በሚገባ ማሰብን ተለማመዱ፡፡ አንድ ጊዜ ይህንን ልምምድ በሚገባ መለማመድ ከጀመርንና ከአንድ ስሜት በኋላ ወደተግባር ከመግባታችን በፊት የሚከተለውን ውጤት ጥጉ ድረስ ማሰብ ከጀመርን ከብዙ ስህተትና ጸጸት እንድናለን፡፡
ዛሬ በስሜት ለማድረግ የተነሳሳችሁበትን ነገር በመረጋጋት ከውጤቱ አንጻር በማሰብ ረገብ ለማለት ሞክሩ!
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ
©Dr. Eyob Mamo
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን