ታንክ ማራኪው ጀግና ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ አረፉ!!

Reading Time: < 1 minute
ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በ72 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ጀግናው አሊ በርኬ የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩ ሲሆን ፥ እናት ሀገር ተወራለች ዝመት በተባሉበት የልጅነት ዕድሜያቸው የሀገራቸውን ዳር ድንበር ለማስከበር እና ወራሪውን የዚያድባሬን ጦር ለመመከት ከእኩዮቻቸው ጋር ዘምተዋል።

የሶማሊያው ዚያድባሬ ጦር እስከ አፍንጫው ታጥቆ የመስፋፋት ህልሙን ለማሳካት ኢትዮጵያን ሲወር፥ አሊ በርኬ እና ጓደኞቻቸው ግንባር በመዝመት ምንጊዜም የሚታወሰውን የካራማራ ጦርነት በድል ተወጥተዋል።

በወቅቱ የዚያድባሬን ወረራ ለመመከት የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም፥ ሚያዚያ 4 ቀን 1969 ዓ.ም የእናት ሀገር አድን ጥሪን አውጀው ነበር።

ጀግናው ሻለቃ አሊ በርኬም ጥሪውን በመቀበል ከቀድሞው ወለጋ ክፍለ ሀገር አሶሳ አውራጃ ቤጊ ወረዳ ወደ ኦጋዴን ዘምተዋል።

በዚህም በኦጋዴን አቡሸሪፍ ግንባር በተደረገ ከባድ ውጊያ የወራሪውን የሶማሊያ ሀይል ቲ-55 ታንኮች በእጅ ቦምብ ደጋግመው በማጋየት ማርከው ትልቅ ጀብድ ሰርተዋል።

በዚህ ጦርነት ኢትዮጵያ በእነ አሊ በርኬና ሌሎች ጀግና ኢትዮጵያውያን ታላቅ ተጋድሎ በታላቁ የካራማራ ድል ሉዓላዊነቷን አስከብራ ቆይታለች፡፡

በጦር ሜዳ ግብራቸውም ጀግና ተብለው የኒሻን ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

ሆኖም ይህ ሽልማትና ክብር ብዙ አልቆየም ፤ ኢትዮጵያን ከወራሪ ሀይል ለመታደግ የተጋደሉት ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ታስረው ቤተሰባቸውም ተበተነ፡፡

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ አሊ በርኬ እስር ቤት ከዘጠኝ ዓመት በላይ በእስር መቆየታቸውም ግድ ሆነ፡፡

ከእስር ሲወጡም የሚገባቸውን ክብር ሳያገኙ መቆየታቸውና የሰሩትን ያክል ሳይሆን ተቃራኒ ህይወት ማሳለፋቸው ይነገራል ፡፡

በቦምብ ታንክ ማራኪው የካራማራው ጀግና ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ በዛሬው እለት በ72 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

54170cookie-checkታንክ ማራኪው ጀግና ሻለቃ ባሻ አሊ በርኬ አረፉ!!

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE