የስልኬ ጥሪ ነው ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ። ከንጋቱ 12:10
“ከሆስፒታል ነው የምንደውለው!! ዶክተር ፈቃደ እባላለሁ።”
“በየሱስም! እናቴ ምን ሆነች?” ብድግ ብዬ ቁጭ አልኩ:: ማታ ስኳሬ ከፍ ብሏል ስትለኝ ነበር።
“ወይዘሮ ሄለን አበራ አደጋ ገጥሟቸው ….”
“ሄለን አበራ? በስመአብ! (ልቤ ጉሮሮዬጋ ደርሳ ነበር ምልስ ብላ አቃፊዋ ውስጥ ስትገባ ታወቀኝ) ምነው እያጣራችሁ ብትደውሉ? በዚህ ጠዋት ያልታመምኩትን ሴትዮ በድንጋጤ ልትገሉኝ ነው እንዴ? ተሳስታችኋል!! እኔ ሄለን አበራ የምትባል ሴት አላውቅም! ”
“ወይዘሮ ፌቨን አዳነ አይደሉም?”
“ነኝ!” አሁን ግራ ገባኝ። ስልኬን ቢሳሳት ስሜን ግን አስተካክሎ ሊጠራ አይችልም።
“የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ተብለው የተመዘገቡት እርሶ ኖት!” ከአልጋዬ በደመነፍስ ወረድኩ
“እህ እኔ እንዲህ የምትባል ሴት አላውቅማ? ቆይ የሆነውን አስረዳኝ ምን አይነት ሴት ናት? ምን አይነት አደጋ ነው የገጠማት?”
“የመኪና አደጋ ነው። ለጊዜው conscious አይደለችም:: ቦርሳዋ ውስጥ ባገኘነው መታወቂያ ላይ የእርሶን ስልክና ስም ነው ያገኘነው።”
“እሺ መጣሁ!” አልኩኝ ነገሩ ምንም ስሜት ሳይሰጠኝ ….. አደጋ ደርሶ ነው እየተባልኩ ከዛ በላይ ጥያቄ ማብዛት ክፋት ነገር መሰለኝ። የእኔን ስም የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ብሎ ሊመዘግብ የሚችል ዘመድ አሰብኩ …….. ምናልባት በቤት ስሟ የማውቃት ዘመድ ….. ጭንቅላቴ እዚህም እዛም እየረገጠ የተባልኩት ሆስፒታል ደረስኩ እና የተባለውን ዶክተር አገኘሁት። የተባለችው ሴት የተኛችበት ክፍል ወሰደኝ። ሰውነቷ በአብዛኛው በፋሻ ስለተጠቀለለ የማውቃት ሴት እንኳን ብትሆን መለየት አልችልም ነበር።
“የማውቃት አይመስለኝም!” አልኩት ግራ ገባቶኝ። ከጋውን ኪሱ መታወቂያዋን አውጥቶ ሰጠኝ። ሲገለባበጥ ሌላ ምስል ያሳየኝ ይመስል እያገለባበጥኩ አየሁት። በፍፁም አላውቃትም! ስሜና ስልክ ቁጥሬ ግን የመታወቂያው ጀርባ ላይ ቁልጭ ብሎ ተፅፏል። እድሜ 30 …. ቆንጅዬ ወጣት ናት። ፎቶዋ ላይ ጥርሷን ሳትገልጥ ፈገግ ብላለች። በወፋፍረሙ ተገምዶ ደረቷ ላይ የተዘናፈለ ፀጉር አላት ….. በፍፁም አይቻት አላውቅም።
“ማነው ሆስፒታል ያመጣት?” አልኩኝ ትክክለኛ ጥያቄ ይሁን ሳልረዳ
“አደጋ ያደረሰባት ሰው ነው ይዟት የመጣው። መጠበቂያ ክፍል ተቀምጧል ልታገኚው ከፈለግሽ? ” ብሎ መልሴን ሳይጠብቅ በሩን ከፍቶ ወጣ ተከተልኩት የተባለው ሰው ከዶክተሩ ጋር ወደክፍሉ ስገባ ሲያየኝ ዘሎ ከመቀመጫው ተነሳ ….. አጠገቡ ተቀምጦ የነበረ በግምት የ4 ዓመት የሚሆን ህፃንም ተከትሎት ብድግ አለ።
“ቤተሰቧ ነሽ? ምን ማድረግ እንደነበረብኝ አላወቅኩም ነበር! እጄን ለፖሊስ ልስጥ? እሰጣለሁ በቃ! (መላ አካሉ ይንቀጠቀጣል።) ከየት መጣች ሳልላት ነው ዘው ብላ የገባችብኝ በቦታው የነበረ ሰውም አልነበረም። አልነጋምኮ …. የሞተች መስሎኝ ነበር !” ድንጋጤው እንዳለ ነው የለበሰው ጥቁር ሱፍና ነጭ ሸሚዝ በደም እንደተነከረ ነው። እጆቹ ላይ የቀረውን የደረቀ ደም ሊጠርገው ግድ ያለው አይመስልም ወይም ከነጭራሹ ደም እጁ ላይ መኖሩንም አላስተዋለውም። ግራ ገባኝ። ምንም በማላውቀው ክስተት ውስጥ የተነከርኩት እኔ ምን ልበል? አይኖቼ ህፃኑ ላይ መንቀዋለላቸውን ሲያይ
“ልጇ ነው። አብረው ነበሩ። እማ ብሎ ሲጮህ ነው ያየሁት እኔ እንጃ ምን እንደተፈጠረ። እሱ የእግረኛ መንገድ ላይ ነበረ። ቤተክርስቲያን እየሄዱ መሰለኝ ነጠላ ለብሳ ነበር። …. ቤተክርስትያን ለመሄድ ራሱ በቅጡ አልነጋም ነበር:: ”
ምን እንደማደርግ ሳላውቅ ህፃኑጋ ተጠግቼ በርከክ አልኩ። ደነበረ። ትንንሽ እጆቹን ልይዛቸው እጄን ስዘረጋ ሰበሰባቸው።
“ስምህ ማነው?” አልኩት እናቱን መኪና ሲገጫት በአይኑ ካየ ሁለት ሰዓት ላልሞላው ህፃን የእኔ ጥያቄ ምኑ ነው? እኔስ ምኑ ነኝ? ዓለምስ ራሱ ምኑ ናት?
“ባባ” አለኝ የደረቁ ከንፈሮቹን እያላቀቀ
“ባባዬ እኔን ታውቀኛለህ?” አልኩት የማይጠየቅ ጥያቄ እንደሆነ እያወቅኩ። በአሉታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ።
“አባትህ የት እንደሆነ ታውቃለህ?” አሁንም በአሉታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ። ግራ ገባኝ! ይህቺ ሴት ማናት? ለምንስ ነው የማላውቃት ሴት መታወቂያ ላይ የእኔ ስም የሰፈፈረው?
“ዶክተር እሷ ያለችበትን ሁኔታ ንገረኝ? ትድናለች አይደል? ” እንድከተለው ምልክት ሰጥቶኝ ወደ ቢሮ ይዞኝ ሄደ። ያለችበት ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ለመገመት አልተቸገርኩም።
“ተጨማሪ ምርመራዎች አዝዣለሁ። ውጤቶቹ እስኪመጡ እርግጠኛ የሆነ ምላሽ ልሰጥሽ አልችልም። ጭንቅላቷ በሃይል ተጋጭቷል። እንዳልኩሽ ሁሉም ውጤት ሳይመጣ ብዙም ማለት አልችልም።”
“የምትድን ይመስልሃል ግን? የምትነቃ ይመስልሃል?”
“ይቅርታ ይሄን አሁን መናገር አልችልም።”
“እሺ እኔ ምን ላድርግ? አላውቃትምኮ? ህፃኑንስ ምን ላድርገው? ምን ጉድ ውስጥ ነው የገባሁት?”
“የማታውቂያት ከሆነ ሆስፒታሉ ለፖሊስ የማሳወቅ ግዴታ አለበት” አለኝ። አላውቃትም ያልኩትን ግን ያመነኝ አይመስልም።
“እሺ የገጫትስ ሰውዬ?”
“ቤተሰብ ቢገኝ ወይ በሽምግልና ያልቃል ወይ ይከሱታል። እንደምትዪው የማታውቂያት ከሆነ ጉዳዩን ለፖሊስ ማሳወቅ ግዴታችን ነው። ሰውየው የማምለጥ ሀሳብ የለውም። ሲገጫት ማንም አላየውም ጥሎ መሄድ ይችል ነበር። ይልቅስ ያላነሰ ብር ከፍሎ የግል ሆስፒታል ሊያሳክማት ፈቃደኛ ከሆነ በህግ ይዳኝ በሽምግልና ቤተሰብ ነው የሚወስነው።”
ሁሉንም ጥዬ መሄድ ፈለግኩ። ምን አገባኝ እና ነው እዚህ ጣጣ ውስጥ የምገባው ብዬ ….. ወደመጠበቂያው ክፍል ስመለስ ህፃኑ የምስራች የምነግረው ይመስል ከተቀመጠበት ዘሎ ተነስቶ በተስፋ አይን አይኖቼን ሲያየኝ እግሬ የሚቀጥለውን እርምጃ መራመድ አቃተው:: አጠገቤ ደርሶ ትንሽዬ ፊቱን ወደ ላይ አንጋጦ እያየኝ ሊያለቅስ ጉንጩ እየተንቀጠቀጠ
“እማዬስ?” አለኝ:: እንባው ከፊደሎቹጋ ከአይኑ እየወረደ….. ከሱ ብሼ እንደህፃን ማልቀስ አማረኝ:: አቅፌ ብድግ እያደረግኩት በዛች ቅፅበት አብሬው እማገዳለሁ እንጂ እሳት ውስጥ ጥዬው እንደማልሄድ አወቅኩ። …
ይቀጥላል ……..
539700cookie-checkአታምጣው ስለው …. አምጥቶ ቆለለውno