ኢትዮጵያዊያን ቲክቶከሮች ሊሸለሙ ነው !

Share Post ►

ሁለት ሚሊዮን ብር ለሽልማት የተመደበለት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የቲክ ቶክ ፈጠራ አዋርድ የፊታችን
ሕዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው ስካይ ላይት ሆቴል እንደሚከናወን አዘጋጆቹ ዛሬ በራማዳ አዲስ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳወቁ።

ሽልማቱ የወጣቶችን ፈጠራ ለማበረታታት የታሰበና ማሕበራዊ ሚዲያውን ለመጥፎ መጠቀም እንዲቀንስ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ውድድሩ በ13 ዘርፎች የሚከናወን ሲሆን ከእነዚህ መካከልም አስቂኝ ቪዲዮ፣ ምርጥ ዳንስ፣ አርትና ኤዲቲንግ፣ ሙዚቃ ፣ ምርጥ አርቲስት፣ የአመቱ በጎ አድራጎት፣ የአመቱ ምርጥ አቅራቢ፣ የሚሉ ይኙበታል። እንዲሁም የአመቱ ምርጥ ቲክ ቶከር የተሰኘ ሽልማትም ይኖራል።

ዩኒየን ኢቨንትስ ያሰናዳው በቲክ ቶክ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ከ10 ሺ ጀምሮ እስከ 250ሺ እና ከዛ በላይ ተከታይ ያላቸው የሚሳተፉበት የሽልማት መርሐግብር ሲሆን የሽልማት ስነስርዓቱ ለኢትዮጵያ ጥሩ ገፅታን የሚፈጥር እና በችሎታቸዉ ሀገርን በጥሩ ስም ማስጠራት የሚችሉ እንዲሁም ሰላምን በዲጂታል መረብ የሚያስተዋውቁ ወጣቶችን ለማበረታታት ያለመ መሆኑን አዘጋጆቹ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

በተለያዩ ምድቦች ውስጥ ከ1280 በላይ የሚሆኑ ቲክቶከሮች በዌብሳይት አማካኝነት መታጨታቸውን እና ከእነሱም መካከል100 የቲክ ቶክ ተፅእኖ ፈጣሪዎች የሚመረጡ ሲሆን የተመረጡት ዝርዝር ቅዳሜ ህዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም ለሽልማቱ ተብሎ በተከፈተው ድህረ ገጽ www.tiktokcreativeawards.com ላይ ይገለጣል።

የምርጫው ሂደት፣ 70 በመቶ ህዝብ ድምጽ የሚሰጥበት ሲሆን ቀሪው 30 በመቶ በዳኞች በኩል ተፈጻሚ ይሆናል።

Share Post ►

Trending Today

You may also like

Leave a Comment

* By using this form you agree you are responsible for what you comment.