ቦንቴል ሞባይል 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ።

Share Post ►

ቦንቴል የተባለው የፊውቸር ፎን አምራች ኩባንያ የተመሰረተበትን አምስተኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ትናንት ጥቅምት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ሳሪስ አዲስ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው አዲስ አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከድርጅቱ ሰራተኞች እና ከደንበኞቹ ጋር በድምቀት አከበረ።

በአሁኑ ወቅት ከ80 በላይ ለሚሆኑ የድርጅቱ ሰራተኞች ቀጥታ የስራ እድል ከመፍጠሩ ባሻገር በመላው ኢትዮጵያዊ የቦንቴል ሞባይል ስልኮችን በማከፋፈል እና በመሸጥ ሰፊ የስራ እድል መፍጠሩን የድርጅቱ የፋይናንስ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዴክ ሙክታር በስፍራው ለተገኙት መገናኛ ብዙሃን ተቋሟት በሰጡት ማብራሪያ ላይ ገልጸዋል።

ቦንቴል ሞባይል እስካሁን ያመርት የነበረው ፊውቸር ሞባይሎችን ሲሆን በቅርቡ ስማርት ስልኮችን በስፋት አምርቶ ወደገብያ ለማውጣት እንቅስቃሴ መጀመሩን የድርጅቱ ሱፐር ቫይዘር የሆኑት ወይዘሪት ሚቶ ሱፊያን ተናግረዋል።

ቦንቴል ሞባይል ማኀበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት በኩል በርካታ ስራዎችን እየሰራ ሲገኝ አምስተኛ አመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ አዲስ አምባ ቅድመ መደበኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ50 ያክል ለሚሆኑ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶችን ስጦታ ከማበርከቱ ባሻገር የተለያዩ ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።

በአምስተኛ አመት የምስረታ በዓል ላይ ከድርጅቱ ሰራተኞች መካከል በስራቸው ብቁ ታማኝ ሁለገብ የሆኑ እና ቴክኖሎጂውን ተላምደው በስራቸው ብልጫ ያመጡ ሰራተኞች የምስክር ወረቀት ፣ ሜዳልያ እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ቦንቴል ሞባይል አዱሱን እና ዘመናዊዉን ምርቱን በቅርቡ ለደንበኞቹ የሚያስተዋውቅ ሲሆን በአምስት አመት የድርጅቱ ጉዞ ወቅት ተሳታፊ የነበሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን እና ግለሰቦችን በሙሉ አመስግናል።

Share Post ►

Trending Today

You may also like

Leave a Comment

* By using this form you agree you are responsible for what you comment.