በኢትዮጵያ የንግድ ስራዎችን እና የነባር የኢኮሜርስ ላይ የተሳተፉ ድርጅቶችን እድገት ለማፉጠንና በሀገር ውስጥ ያሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በኢኮሜርስ ውስጥ ለማሳተፍ የሚያግዝ የቬንቸር ሜዳ የማሳያ ቀን 2023 የተሰኘ ፕሮግራም ባሰለፍነው ማክሰኞ ጥቅምት 20 ቀን 2016ዓ.ም በኤሊሊ ሆቴል ተካሄዷል።

ከግንቦት 2022 ጀምሮ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ኢሲአዲስ ጋር በመተባበር በኢኮሜርስ ሶልሽን ዘርፍ አዳዲስ ፈጠራን በኢንኩቤሽን እና በአክሰለሬሽን ድጋፍ ለማጎልበት ቬንቸር ሜዳ የተባለ ፕሮግራም በመቅረጽ ሁለት ዋና አላማዎችን ማለትም በኢትዮጵያ የንግድ ስራዎችን እና የነባር የኢኮሜርስ ላይ የተሳተፉ ድርጅቶችን እድገት ለማፉጠንና በሀገር ውስጥ ያሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በኢኮሜርስ ውስጥ ለማሳተፍ ሲሰሩ እንደቆዩ ተገልጿል።

በዚህ ፕሮግራም ያለፉ 20 ኢንተርፕራይዞች አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶቻቸውን በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ የመንግስት አጋሮች (የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር እና ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር) እና ባለሙያዎች፤ ለባለሀብቶች እንዱሁም ለሌሎች ባለድርሻ አካላት አሳይተዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በፕሮግራሙ ላይ በኢኮሜርስ ሶልሽን ዘርፍ ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሄዷል።
ቬንቸር ሜዳ የማሳያ ቀን 2023 በአለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ባለው የኢ-ኮሜርስ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚሳተፉ ንግዶችን የሚደግፍ ፕሮግራም ነው፡፡