የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማህበር የአረጋውያን የህክምና ማዕከል ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ::

Share Post ►

ማህበሩ ለአረጋውያን የህክምና ማዕከል ለመገንባትና በአረጋውያን ሕክምና ዙርያ ሐኪሞች የሚሰለጥኑበትን ተቋም ለመመስረት አላማ ይዞ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሆነ በማህበሩ የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ግርማ ገብረስላሴ  ለአራዳ ኤፍኤም ገልፀዋል::

የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማህበር በዛሬ ዕለት 25ኛ ዓመት በዓሉን አስመልክቶም የተለያዩ መርሃ-ግብሮችን ማዘጋጀቱን አሳውቋል::

ከነገ በስትያ በብሔራዊ ሙዝየም የድርጅቱን የ25 ዓመታት ጉዞ የሚያሳይ የፎቶግራፍ አውድርዕይ ለእይታ ክፍት የሚያደርግ ሲሆን ህዳር 9/2016 ዓ.ም. ደግሞ የገቢ ማሰባሰቢያ ያከናውናል::

ማህበሩ እንጦጦ ኪዳነምህረት አካባቢ ለ18 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ በአሁኑ ወቅት አርባ አንድ ኢየሱስ አካባቢ በሚገኝ ስፍራ እስከ 200 የሚደርሱ ዜጎችን እየረዳ ይገኛል::

@enqu(እንቁጣጣሽ ኃ/ማርያም )

Share Post ►

Trending Today

You may also like

Leave a Comment

* By using this form you agree you are responsible for what you comment.