🎯 አብሮነት መሻል ነው!
ዶ/ር ጋሻው አብዛ
የግራንድ አፍሪካ ረን ዳሬክተር
♦አምስተኛዉ ግራንድ አፍሪካን ረን በዲሲ በመጪዉ ኦክቶበር 12 ይካሄዳል
♦በርካታ ኢትዮጵያዊያን ኦሎምፒያኖች እና የዓለም ሻምፒዮኖች በዚህ ዝግጅት ላይ በክብር እንግዳነት ይሳተፋሉ።
♦የግራንድ አፍሪካን ረን ባለፉት አምሰት ዓመታት ባዘጋጃቸው ሁነቶች ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ አድርጓል፡፡
ዶ/ር ጋሻው አብዛ የግራንድ አፍሪካ ረን መሥራችና (CEO)
ከጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ የተወሰደ
የ2024 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ተሸላሚዎች ይፋ ሆነዋል
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ
አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የተመሰረተውና ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖቫ ኮኔክሽን የሚያዘጋጀው የ2024 አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ የዘንድሮ የክብር ተሸላሚዎች ታውቀዋል።
ይህ አመታዊ የእውቅና ሽልማት ስነ ስርአት በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የተዘጋጀ ነው። በየአመቱ ከስፖርት፣ ከስነ ጥበብና ከስራ ፈጠራ ዘርፎች ለማህበረሰቦቻቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦና ለለውጥ ላደረጉት የላቀ ተሳትፎ ከየዘርፉ ተመርጠው የሚሸለሙበት መድረክ ነው።
አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ እስካሁን ለአራት ጊዚያት ተካሂዷል።
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
📌 2019: ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ( ቴዲ አፍሮ )፣ አትሌት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉና ሚስተር ማርክ ጌልፋንድ
📌 2020 – በኮቪድ-19 ምክንያት አልተካሄደም!
📌 2021- አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ ድምፃዊ ኤኮንና አቶ በረከት ወልዱ
📌 2022 – አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ “እረኛዬ” የቴሌቪዥን ድራማ፣ አቶ ሄኖክ ተስፋዬ እና ንግሥት ሰናይ ልኬ
📌 2023 – የዲባባ ቤተሰብ፣ አቶ ግርማ ዋቄ፣ አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄና አትሌት ስለሺ ስህን
ዘንድሮም በተለያዩ ዘርፎች አምስት ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያንን ለማክበርና እውቅና ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቋል።
የዚህ አመት ተሸላሚዎች በሙሉ ሴቶች ናቸው።
በስነ ጥበብ ዘርፍ:-
❣️ዝነኛዋ ድምፃዊት አስቴር አወቀ
በጋዜጠኝነት
❣️ አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ፣
በስፖርቱ ዘርፍ የማራቶንና የ5000 ሜትር የአለማችን ክብረወሰን ባለቤቶች:-
❣️ ትዕግስት አሰፋ
እና
❣️ ጉዳፍ ፀጋዬ
በቢዝነስ ዘርፍ:-
❣️ ርብቃ ሀይሌ ተሸላሚዎች ይሆናሉ።
በእለቱ የዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ሴናተሮች፣ ከንቲባዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረጋላቸው በርካታ እንግዶች ይገኛሉ፤ ተሸላሚዎቹ ከግዛቶቹና ከተማዎቹ ተወካዮች የእውቅና ሰርተፍኬት ይበረከትላቸዋል።
በተጨማሪ ለበጎ አድራጎት ሥራ የሚውል የሙዚቃ ዝግጅት በወጣቷ ድምፃዊት ራሄል ጌቱና በታዋቂው መሳሪያ ተጫዋች ሰላም ስዩም የሚቀርብ ይሆናል።
የ2024 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ስነ ስርአት ሜሪላንድ በሚገኘውና ኢትዮጵያዊያን በባለቤትነት በሚያስተዳድሩት ሜትሮ ፖይንትስ ሆቴል እሁድ ኦክቶበር 13 ቀን 2024 ምሽት በደማቅ ዝግጅት ይካሄዳል።
🎯 አብሮነት መሻል ነው!
Chance to win ❣️♦📌
የ2024 ቶዮታ ኮሮላ መኪናዎን ይውሰዱ
ለውድድሩ የሚመዘገቡ ተሳታፊዎች በሙሉ በእጣ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን፣ እድለኛው አሸናፊ በዝግጅቱ ቀን ማብቂያ ላይ የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓቱ ተከናውኖ በይፋ ይገላጻል።
በዘንድሮው ግራንድ አፍሪካን ረን በዲሲ ሲሳተፉ፣ የ2024 ቶዮታ መኪና ዕጣ የማግኘት ዕድል ይኖርዎታል።❣️♦📌
ለመመዝገብ www.africanrun.com ይጠቀሙ።
የመኪናው ሽልማት፣ ስፖንሰሮቻችን ዳሸን ባንክ እና አሌክዛንደሪያ ቶዮታ በአዘጋጆቹ በኩል ያቀረቡት ነው።
ግራንድ አፍሪካን ረን ለሁሉም ሰው ክፍት ነው – ጀማሪ ሯጭ ይሁኑ፣ ፕሮፌሽናል።
በርምጃ፣ በሶምሶማ ውይም በሩጫ ርቀቱን ሊያጠናቅቁ ይችላሉ።
ዝግጅቱ ከሩጫም በላይ ነው።
ማህበረሰባችን ተሰባስቦ አብሮነታችንን የምናክብርበት ቀን ነው።
ግራንድ አፍሪካን ረን ቀኑ ቀረበ – ኦክቶበር (Oct) 12 ። ይመዝገቡ፣ ከወገንዎ ጋር ቀኑን ያሳልፉ፣ ይዝናኑ፣ ይሸለሙ። ውሱን ቦታዎች ናቸው የቀሩት ቀድመው ይመዝገቡ። ለመመዝገብ www.africanrun.com ይጎብኙ።
African Grand Run – 🇺🇸
ቦታ፦ ዋሽንግተን ዲሲ
ቀን፦ ኦክቶበር 12 ጠዋት 9:00am
በዝግጅቱ ለመታደም ትኬትዎን የሚከተለውን ሊንክ በመከተል ያገኛሉ: https://shorturl.at/YQvrv
For more: Nova Connections, Email: helenah@africarun.com; https://www.africanrun.com/impact
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን) – ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ – በኖቫ ኮኔክሽን የሚዘጋጁ ( የአፍሪካን ኢምፓክት አዋርድ እና የግራንድ አፍሪካን ረን ) ዝግጅቶች የኢትዮጵያ ወኪል ነው።
Getu Temesgen Media & Comminucations
is sole agent in Ethiopia for African Impact Award and Grand African Run events organized by Nova Connection.