ልጅዋን በግፍ የተነጠቀችሁ እናት የመኖርያ ቤት ተሰጣት፡፡
ሰሞኑን በህፃን ሄቨን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ድርዲት ተቃውመዋል የሄቨንን እናት አፅናንተዋል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ የሄቨን እናትን በማግኘት አጽናንተዋል::
ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትህ ሳታገኝ ለቆየችው እህታችን የፍትህ ሂደቱን ለመከታተል ፣ ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆንላት እና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲመች የከተማ አስተዳደሩ አንድ የመንግስት የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በሙያዋ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንድትሰራ መመቻቸቱን ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል::
የህፃን ሄቨን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ ተገቢውን ፍትህ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋፅዖ ያለው ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች የዚህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም የማህበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ እና ችግሩ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል::
@yenevibe.com