በአማራ ክልል
18 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ወደ ፓሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አደጉ
#Ethiopia | በአማራ ክልል 18 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተሻለ ክህሎትና ሙያ ያለው የሰው ሃይል ማፍራት እንዲችሉ ወደ ፓሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ደረጃ እንዲያድጉ መደረጉን የክልሉ ስራና ስልጠና ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ስራና ስልጠና ቢሮ ወደ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ላደጉ ኮሌጆች እውቅና የመስጠት ፕሮግራም በኮምቦልቻ ከተማ አካሂዷል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አማረ ዓለሙ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጉትን የሰለጠነና እጁ የተፍታታ የሰው ሃይል በማፍራት ረገድ የጎላ ሚና አላቸው።
ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠልም በሰው ኃይል፣ በግብዓት፣ በአካባቢ የሰልጣኞች ቁጥር ፍላጎትና ሌሎችንም መስፈርቶች አሟልተው የተገኙ 18 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ወደ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ እንዲያድጉ መወሰኑን ገልፀዋል።
በዚህም ቀደም ሲል እስከ ደረጃ 4 ብቻ ያሰለጥኑ የነበረውን እስከ ደረጃ 5 ማሰልጠን እንዲችሉ እድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም ደረጃ 5 ለመስልጠን ወደ ሌላ ከተማና አካባቢ ይሄዱ የነበሩ ሰልጣኞችን ችግር ከማቃለሉም በላይ የተሻለ ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት ብቁና ክህሎት ተኮር ስልጠና ለመስጠት የሚያስችሉ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
በክልሉ 126 የመንግሥት ማሰልጠኛ ኮሌጆች ሲኖሩ ዛሬ ያደጉትን ጨምሮ 42 ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንዳሉም ተመላክቷል።
የመካነ ሰላም ከተማ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲን አቶ ምስጋናው እጅጉ በበኩላቸው፤ ኮሌጁ ማደጉ በተሟላ ግብዓት ተግባርና ክህሎት ተኮር ስልጠና ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።
በአካባቢው የሰልጣኝ ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም ደረጃው ባለመፍቀዱ ሰልጣኞች ይቸገሩ እንደነበረ አስታውሰው፤ አሁን ደረጃው መሻሻሉ በርካታ ሰልጣኞችን ለመቀበል እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
በዚህም ቀደም ሲል እስከ ደረጃ 4 ብቻ ስልጠና ወስደው የተቀመጡ ሰልጣኞችን በደረጃ 5 ጭምር ለማሰልጠን ግብዓት የማሟላት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በመድረኩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የከተማና መሰረት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አህመዲን መሐመድን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞንና የከተማ የሥራ ሃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ከእውቅና አሰጣጡ ጎን ለጎንም የስራና ስልጠና ቢሮው የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።#ኢዜአ
Source
1505500cookie-checkበአማራ ክልል
18 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ወደ ፓሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አደጉ
#Ethiopia | በአማራ ክልል 18 የቴክ…no