የአይምሮ እድገት ውስንነት ቀንን አስመልክቶ የሩጫ መርሐ-ግብር መዘጋጀቱ ተገለፀስለ ሲፒ ጉዳት ይመለከተኛል…

Reading Time: < 1 minute
*
የአይምሮ እድገት ውስንነት ቀንን አስመልክቶ የሩጫ መርሐ-ግብር መዘጋጀቱ ተገለፀ

ስለ ሲፒ ጉዳት ይመለከተኛል በሚል በዛሬው እለት በእዝነት አካል ጉዳተኛ ህጻናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት ውስጥ የግንዛቤ ማስጨበጥ መርሐ-ግብር የተካሄደ ሲሆን  ይህን አስመልክቶ የፊታችን መስከረም 26 የእግር ጉዞ መርሐ-ግብርም መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ይህንንም የእግር ጉዞ ይፋ ለማድረግ እና የቲሸርት ምረቃ መርሐ ግብር የተካሄደ ሲሆን 10000 የሚሆኑ ቲሸርቶች መዘጋጀታቸው ተገልጿል።

ቲሸርቱ ከዛሬ ጀምሮ ለሽያጭ የቀረበ ሲሆን የአንዱ ቲሸርት ዋጋ 400 ብር ነው ትብሏል
የCP ጉዳተኛ ህፃናት ራሳቸውን ችለው መቀመጥ፥ መቆም፥ መመገብ፥ ንፅህናቸውን መጠበቅ፥ መናገር አንዳንዱም ማየት የማይችሉ፥ እዲሁም በየቀኑ በተደጋጋሚ seizure የሚከሰትባቸው ህፃናት ናቸው።

እዝነት እነዚህ ህፃናት እንደማንኛውም ዜጋ ማግኘት ያለባቸውን እንከብካቤ እያገኙ ጤንነታቸው እና ምቾታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ የሚጥር ማእከል እንደመሆኑ መጠን የCP ጉዳት ምንነትን አስመልክቶ የማሕበረሰቡ ግንዛቤ ከፍ እንዲል ለማድረግ የአይምሮ ውስንነት ቀንን (CP-day) ተንተርሶ ይህን የእግር ጉዞ መርሐ-ግብር ለማዘጋጀት መዘጋጀቱን የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘቢባ አህመድ ገልጸዋል።

ወ/ሮ ዘቢባ አክለው እንደገለጹት ህብረተሰቡ በሐገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የአለም ሴሬብራል ፓልሲ ቀንን በማስመልከት በተዘጋጀው በዚህ የእግር ጉዞ መርሐግብር ላይ በመሳተፍ ለአካል ጉዳተኛ ህጻናት በተለይም ለሲፒ ጉዳተኛ ህጻናት አለኝታ በመሆን ከድርጅቱ ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል።
150120cookie-checkየአይምሮ እድገት ውስንነት ቀንን አስመልክቶ የሩጫ መርሐ-ግብር መዘጋጀቱ ተገለፀስለ ሲፒ ጉዳት ይመለከተኛል…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE