አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃ እና ሙዚቃዊ ጉዳይ በወሩ ምርጥ የሙዚቃ አልበም እንጋብዛችኃለን፡፡
-ሄኖክ ክብሩ(ራስ ጎፈር) – ”ተወኛ” የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ይዞ እየወጣ ይገኛል በግጥም ዜማ እራሱ ሄኖክ ክብሩ በቅንብሩ ሱራፌል የሺ ጥላ ሰርተውታል በቅርብ በናሆም ሪከርድስ በኩል ይለቀቃል፡፡
-ሳሚ ዳን -“ከዓይኔ ላይ ነው” የተሰኘ ሙዚቃ እንደ ገና በሩፍ ታፕ ስቱዲዮ የሁለተኛ ዙር ስራ ሙዚቃውን ሰርቶታል በቅርቡ በሳሚ ዳን ዮትዮብ ቻናል ጠብቁ፡፡
-እስጢፋኖስ ቶማስ-”እኔን ብሎ አኩራፊ” በተለያዩ ሙዚቃዎች የሚታወቀው በተለይ ቲክቶክ ላይ እራሱን እያስተዋወቀ የሚገኘሁ በአዲስ ነጠላ ሙዚቃ እየመጣ ይገኛል አርብ ማታ በሆፕ እንተርቴመንት በኩል ይደርሳል ተብሏል፡፡
-”እንቁጣጣሽ ኮንሰርት” አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በጂ-ፓወር አማካኝነት ጿጉሜ ሁለት የአዲስ አመት መቀበያ ኮንሰርት በዱባይ ያከናውናል በዝግጅቱ ላይ አንጋፋ እና ወጣት ሙዚቀኞች ይሳተፋሉ ንዋይ ደበበ ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ አብርሀም ገብረመድህን ፣ አንዱዋለም ጎሳ ፣ ዮሐና አሸናፊ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል መግቢያው ከሶስት መቶ ድርሀም ጀምሮ ነው ብሏል፡፡
* የሚወጡ አልበም ጥቆማ እናድርሳትችሁ
-ሚካኤል በላይነህ ድምፃዊ ” አራተኛ አልበሙ” በቅርብ ቀን ያደርሰናል፡፡ ይህ አልበም መጠርያ ስሙ “አንድ ቃል” ይሰኛል፡፡ተወዳጁ ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ አራተኛ አልበሙን ለሙዚቃ አድናቂዎች በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚለቅ የተገለፀ ሲሆን ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ የመጀመርያ አልበም ስራው ከግርማ ይፍራሸዋ ጋር የሰራው “መለያ ቀለሜ” የተሰኘው በመቀጠል አንተ ጎዳና ከኤልያስ መልካ ጋር እና ፍቅር እና ናፍቆት ከሚካኤል ሀይሉ ፣ ቴዲ ማክ ፣ ኩሩቤል ተስፋዬ ፣ አበጋዝ ክብረ ወርቅ በጋራ አድርሰውናል፡፡ አራተኛ አልበሙ በራሱ ዩትዮብ ቻናል አልበሜን በቅርቡ ጠብቁ ብሎናል፡፡
-የተወዳጁ ፕሮዲውሰር እና የራፐር የሙዚቃ አቀንቃኝ ልጅ ሚካኤል ታዬ(ልጅ ማይክ ) ሶስተኛ አልበሙን በቅርብ ቀን” አዲስ አራዳ” የተሰኘ የሙዚቃ አልበም እንደ ሚያደርሰን በራሱ ማህበራዊ ገፅ ላይ ገልጿል፡፡ከዚህ ቀደም ከአቀናባሪ ድራም ተጫዋች ከሁን አንተሙሉ ጋር ”ዛሬ ይሁን ነገን” በመቀጠል ከ አቀናባሪ ዮናስ ነጋሽ ጋር “አትገባም አሉኝ” አድርሶናል፡፡ በቅርብ ደግሞ አዲስ አራዳ ሲል ለህዝብ ያደርሰናል፡፡
– የአንጋፋው የጉራጊኛ ሙዚቃ ተጫዋች፣ ዜማ ደራሲና ገጣሚ አርቲስት ፀጋዬ ስሜ 7ኛ የሙዚቃ አልበም በአዲስ አመት ዋዜማ ሊያደርሰን ቀን ቆርጧል፡፡ከዚህ ቀደም ”ክስታኔ ባንድ፣ ኬር ዬሁን፣ ኦሴባሳ(ባላገር)፣ ዬሻልቢ፣ ጥንቡሳሳም እና ሱታና” በተሰኙ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበም ሥራዎቹ የሚታወቀው አርቲስት ፀጋዬ ስሜ አሁን ደግሞ ለአዲስ አመት በአዲስ መንፈስ ሰባተኛ አልበሙን ”#ቡርሻት” ሲል ሰይሞታል፡፡
-ድምፃዊ ምስክር አወል የግጥምና ዜማ ደራሲ የሆነው አዲስ የአልበም ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።ከ1990ዎቹ መጨረሻዎቹ ዓመታት ብቅ ብለው የተለያዩ ነጠላ ሙዚቃዎችን የሚሰጡን ከነበሩ ተወዳጅ ድምፃውያን መካከል አንዱ የነበረው ምስክር አወል አዲሱ የአልበም ስራው በርካታ .ከያኒያን የተሳተፉ ሲሆን አንጋፋዎች ኤልያስ መልካ እና ዳግማዊ አሊ የተጣመሩበት በቅርቡ እንደ ሚደርስ ገልጿል፡፡
* በዚህ ሳምንት ከተሰሙ ሙዚቃዊ ጉዳይ
-ድምፃዊ ዮሐና አሸናፊ ካሴት የኦድዮ የብራንድ አምባሳደር ሆኖ የተሾመበት ነበር፡፡ሐምሌ 29/2016 በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል፡፡ አርቲስቶች አድማጮች የገዙትን አልበም በሌሎች መላክና መስጠት የሚስችል መሆኑ እና የኮፒ ራይት ጉዳይ ይከላከላል ተብሏል፡፡
-የተወዳጅዋ አስቴር አወቀ ልታቀርበው የነበረው ኮንሰርት መሰረዙ ነው በአውሮፖ የኢትዮጲያ ስፖርት ባህል ፌደሬሽን ያዘጋጀው የ2024 አመታዊ እግር ኳስ ውድድር የመዝግያ ውድድር የአስቴር አወቀ ኮንሰርት በተፈጠረ የአዳራሽ ሳውንድ ችግር ምክንያት ፕሮግራሙ ሙሉ በሙሉ መሰሩዙ የተሰማበት ሳምንት ነበር፡፡
-ሙዚቃዊ የፐብሊሺንግ ከ አንጋፋዎቹ የአቤክስ ባንድ መስራቾች ጋር ተፈራርመዋል ተወዳጆቹ የቤዝ ጊታር ተጫዋች ጆቫይኒ ሪኮ እና የሊድ ጊታር ተጫዋች ሰላም ስዩም ቀይሮ ለመስራት ስምምነት አድርገዋል፡፡
– ተወዳጁ የግጥም እና ዜማ ደራሲ አብዱ ኪያር ሰሞኑን ሰይፉ በኢቢኤልስ ላይ ባደረገው ቆይታ በርካታቶች ተቀባብለው አይተውታል ወደውታል እጅግ ድንቅ ማራኪ ዝግጅት መሆኑን እና ትምህርታዊ ፣ የሙዚቃ አረዳድ ፣ የትዝታን ማዕበል፣ በማህበረሰብን ወካይ ቋንቋ በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል ፡፡ ድምፃዊ አብዱ ኪያር ያልተሰሙለት ልሰማቸው የሚገባ እንዳሉም በቀጣይ በመፅሐፍ መልክ ለማውጣትም እንደ ታሰበ ድምፃዊው ገልጿል፡፡
– ደማቅ ኮንሰርት የተከናወነበት ሳምንት ነበር የሐረር ቢራን 40ኛ ዓመትን በማስመልከት በውቢቷ ሐረር ከተማ አሚር አቡባ ስቴዲየም ለሚዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ዝግጅታቸውን አርበዋል የምወዳቸውን እና የምናደንቃቸውን አርቲስቶች ድምፃዊ ጊዚ ዛጋ ፣ ቬሮኒካ አዳነ ፣ ፀጋዬ እሸቱ ፣ አንዱዋለም ጎሳ ፣ ሀና ግርማ ተዘጋጅተዋል ቅዳሜ ሀምሌ 27 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅታቸውን በደማቅ አሳልፈዋል ተወዳጅ ድምፃያኖቹ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡
በዚህ ምርጡ የወርሀዊ አልበም ጥቆማ እናድርሳትችሁ ፡፡
የድምፃዊት ዳግማዊት ፀሐዬ ”ወርቅ” የተሰኘ አልበም ነው በፍቅርን ፣ መተሳሰብን ፣ ትዝታን ፣ ሰውኛ በዓሪን ያንፀባርቃል፡፡ በርካታ አንጋፋ ሰዎች የተሳተፉበት በግጥም እና ዜማ ዳና አድማሱ ፣ መሰለ ጌታሁን ፣ሳምሶን ታደሰ ቤቢ ፣ ናቲ ኬር ፣ አቡዲ ፣ ዮናስ ነጋሽ ፣ ማሚላ ሉቃስ ፣ ታምራት ካህሳይ ፣ ዳግማዊ ፀሐዬ ፣ ፍሬዘር አበበ ወርቅ እና ራስ ጎፈር ናቸው በቅንብሩ አቤል ጳውሎስ ፣ ቤካ ግዕህ ፣ ናትናኤል ተሾመ ፣ ዮናስ ነጋሽ ፣ ካሙዙ ካሳ በማስተሪንግ ኪሩቤል ተስፋዬ በዚህ አመት ከወጡ 27 አልበሞች መሀል መርጠን ወደ እናንተ አርሰናል፡፡
አዘጋጅ እና አቅራቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
yenevibe.com ጎብኙን፡፡
-ሄኖክ ክብሩ(ራስ ጎፈር) – ”ተወኛ” የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ይዞ እየወጣ ይገኛል በግጥም ዜማ እራሱ ሄኖክ ክብሩ በቅንብሩ ሱራፌል የሺ ጥላ ሰርተውታል በቅርብ በናሆም ሪከርድስ በኩል ይለቀቃል፡፡
-ሳሚ ዳን -“ከዓይኔ ላይ ነው” የተሰኘ ሙዚቃ እንደ ገና በሩፍ ታፕ ስቱዲዮ የሁለተኛ ዙር ስራ ሙዚቃውን ሰርቶታል በቅርቡ በሳሚ ዳን ዮትዮብ ቻናል ጠብቁ፡፡
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
-”እንቁጣጣሽ ኮንሰርት” አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በጂ-ፓወር አማካኝነት ጿጉሜ ሁለት የአዲስ አመት መቀበያ ኮንሰርት በዱባይ ያከናውናል በዝግጅቱ ላይ አንጋፋ እና ወጣት ሙዚቀኞች ይሳተፋሉ ንዋይ ደበበ ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ አብርሀም ገብረመድህን ፣ አንዱዋለም ጎሳ ፣ ዮሐና አሸናፊ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል መግቢያው ከሶስት መቶ ድርሀም ጀምሮ ነው ብሏል፡፡
* የሚወጡ አልበም ጥቆማ እናድርሳትችሁ
-ሚካኤል በላይነህ ድምፃዊ ” አራተኛ አልበሙ” በቅርብ ቀን ያደርሰናል፡፡ ይህ አልበም መጠርያ ስሙ “አንድ ቃል” ይሰኛል፡፡ተወዳጁ ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ አራተኛ አልበሙን ለሙዚቃ አድናቂዎች በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚለቅ የተገለፀ ሲሆን ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ የመጀመርያ አልበም ስራው ከግርማ ይፍራሸዋ ጋር የሰራው “መለያ ቀለሜ” የተሰኘው በመቀጠል አንተ ጎዳና ከኤልያስ መልካ ጋር እና ፍቅር እና ናፍቆት ከሚካኤል ሀይሉ ፣ ቴዲ ማክ ፣ ኩሩቤል ተስፋዬ ፣ አበጋዝ ክብረ ወርቅ በጋራ አድርሰውናል፡፡ አራተኛ አልበሙ በራሱ ዩትዮብ ቻናል አልበሜን በቅርቡ ጠብቁ ብሎናል፡፡
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ