ጿጉሜ 2 በዱባይ በጂ -ፖውር አማካኝነት ኮንሰርት ሊደረግ ነው

አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ በጂ ፓወር አማካኝነት የተዘጋጀው የ2017 አዲስ ዓመት መቀበያ የሙዚቃ ኮንሰርት በቀጣይ ጷጉሜ 2 ቀን በዱባይ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ወጣት እና አንጋፋ ድምፃዊያን የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ንዋይ ደበበ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ አብርሃም ገብረመድህን፣ አንዱአለም ጎሳ፣ ዮሃና በኮንሰርቱ ላይ የሚገኙ ሙዚቀኞች ናቸው።
የመግቢያ ዋጋ ከ300 ድርሃም ጀምሮ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ከኢትዮጽያ ለሚሄዱ ቪዛ እና ሌሎች አገልግሎት የያዘ ፓኬጅ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ አዘጋጁ በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቋል።
በኮንሰርቱ በትንሹ እስከ አራት ሺህ ሰው ይጠበቃል ያሉት አዘጋጆቹ የአንድ ሰው መግቢያ ትኬት በ300 ድርሀም ጀምሮ እንደ የሚሸጥ ሲሆን ከአንድ ትኬት የመግቢያ ዋጋ ሁለት ድርሀም ለማስተር አብነት ለሚሰራው በጎ አድራጎት ሥራ የሚሰጥ መሆኑን ገልፀዋል።
ጂ ፓወር እንቁጣጣሽ ኮንሰርትን ያዘጋጀው ከአሁን ቀደም የቴዲ አፍሮ ኮንሰርትን በዱባዩ ኮካ ኮላ አሬና ያዘጋጀውና የቴክኖሎጂ እቃዎችን በማስመጣት የሚታወቀው ጂ- ፓወር ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ነው።
ጂ -ፓወር በሶላር እና በኤሌክትሪክ ኃይል መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችሉ ምርቶችን ለደንበኞች በማቅረብ ስራው የጀመረ ሲሆን በአሁን ሰዓት በርካታ የመዝናኛ ስራዎችን እየሰራ ሲገኝ በቀጣይ ህዳር ወር ላይ በኢትዮጵያ ትልቅ የሙዚቃ ዝግጅት እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል።
የሙዚቃ ኮንሰርት የሙዚቃ ባንድ አጃቢዎች መሀሪ ብራዘርስ ከ ድምፃዊያኖቹ ጋር ሆነው የሙዚቃ ስራዎቹን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
yenevibe.com ጎብኙን