“ኬንዲ መንገሻ
የሙዚቃ ልኬት ህሊናንመካሻ”
ከአመታት በፊት ተ/ሀይማኖት ፊትለፊት ያለው አንበሳ ጫማ መደብር ያለበት ህንጻ ሰፊ በረንዳ የጎዳና ተዳዳሪዎች መናሀሪያ ነበር ። እና እዚህ ቦታ ፌስታል ሙሉ ክትፎ ይዞ የሚመጣ አንድ ሰው ነበርይህ ሰው ኬኔዲ መንገሻ ነው ፡፡ ኬኔዲ አንዳንዴ ነሸጥ ሲያደርገው ወደዛ ይሄድና ” ዱርዬ ተሰብሰብ ” እያለ የጎዳና ተዳዳሪዎችን በፍቅር ሰብስቦ በጊዜው ተ/ሀይማኖት ሱማሌ ተራ አካባቢ ዝነኛ ከነበረው ግዛው ክትፎ ቤት ገዝቶ ያመጣውን ክትፎ አብሯቸው እየተሻማ ይበላና የሻይ ሰጥቷቸው ፡ በብርቱካንማ ሬኖ መኪናው ይሄዳል ።
…….
አስገራሚው ነገር ኬኔዲ የትኛውም ታዋቂ ሰው የማያደርገውን ይህን መሳይ ነገር ሲያደርግ. .. በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ዝነኛ ከነበሩ አርቲስቶች መሀከል አንዱ ነው ። ሆኖም ዝናው አንድም ቀን ትከሻውን አጉብጦት አያውቅም ።
…….
አንድም ቀን በኩራት ልቡ ሳያብጥ ፡ አንድም ቀን ላይ ሆኖ አድናቂዎቹን ቁልቁል ሳያይ ፡ የለበሰውን አውልቆ እንደሰጠ ። ተቸገርኩ ላለው ሁሉ ባይኖረው እንኳን. . ተበድሮ እጁን እንደዘረጋ. …. እንደ ክረምት ፀሀይ ብልጭ ብሎ አፍታም ሳይቆይ ይህችን ምድር ተሰናብቶ ሄደ ።
የሰውነት ጥግ ።
ተፃፈ በዋስይሁን ተስፋዬ
****
ድምፃዊ ኬኔዲ መንገሻ (ከ1956 እስከ 1985)
(ሐምሌ 19 ቀን 1985 ልክ የዛሬ 31 ዓመት ነበር በ29 ዓመቱ ድምጻዊ ኬኔዲ መንገሻ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው)
የኬኔዲ አያት የአፄ የኃይለ ሥላሴ የግቢ ባለሙዋል ነበሩ። የአፄ ኃይለ ሥላሴ ወዳጅ የነበሩት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ሲሞቱ ኃይለሥላሴ በጣም ስለአዘኑ ቻርተር አዉሮፕላን ተዘጋጅቶላቸዉ ለቀብር ወደ ዩናይትድ ስቴት ሲሄዱ በዚያን ዕለት ደግሞ ድምፃዊ ኬኔዲ መንገሻ ተወለደ።
Yenevibe.com ጎብኙን፡፡