#ክብር ለታላቁ ንጉሥ ልደት ቀን!”ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሡ!” ይልዎ የነበረው ሕዝብ ምን አይቶ ምን ሰ…

Reading Time: < 1 minute
*
#ክብር ለታላቁ ንጉሥ ልደት ቀን!

“ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሡ!” ይልዎ የነበረው ሕዝብ ምን አይቶ ምን ሰምቶ ምን ተስፋ ሰንቆ ይሆን? እንላለን።

ጃንሆይ በልደትዎ ምክንያት ብዙ ብዙ ትዝ ይለናል።

#ማይጨው ላይ በርስዎ የተመራው ጦር የሙሶሎኒን ጦር አልተቋቋመምና ባናዝንብዎትም አዝነናል።

#ጣሊያን የመርዝ ጋዝ ነስንሶ እንደህዝብ አቃጥሎናል። አሜሪካንና ራሻን ጨምሮ ባይደግፉም ዝም ስላሉ አንድ ሀገር ዘላቂ ነጻነት የምትፈልግ ከሆነ በራሷ እንጂ በማንም ድጋፍ ትቆማለች ብሎ መቀላወጡ አያዋጣም አልን።

#ንጉሣችን – በኋላ ላይ እርስዎ በዘየዱት መላ የሩዝቬልቷ አሜሪካ እንግሊዝ ከምድራችን እንድትወጣ ድጋፍ በማስገኘትዎ፣ ያለ ጦርነት ማሸነፍንም በርስዎ ስላወቅን እናመሠግናለን።

#ተማሪዎችዎ ሲረብሹዎት እንደልጅ አይተው ይከተሉት የነበረው አመራር ለመንበርዎ መነቅነቅ ጉዳት ቢያስከትልም ደግ ንጉሥ ነበሩ።

#ንጉሥ ሆይ ከየትኛውም ዓለም ሀገራት ወደርስዎ የሚመጡትም ሆነ እርስዎ ሲሄዱባቸው የሚታየው የላቀ ክብርዎ ክብራችን ሆኖ ታሪክ መዝግቦታል፤ ስናነበውም እንኮራለን።

#ጃንሆይ ሸሽተውም ሆነ ለዲፕሎማሲ ብለው ከሀገር ሲወጡ እንደሚኒልክ ለምን አልተዋጉም፣ ለምንስ ድል አላደረጉም ብለን ቅር ተሰኝተንም ቢሆን ሁኔታውን እናስታውሳለን። ቢሆንም ግን የሊግ ኦፎ ኔሽንስ ንግግርዎ አንጀት አርስ ነበር። ዛሬ በኛ የሆነው ነገ በእናንተ ይሆናል አሏቸው። ወሬ ሆኖ ሳይቀር ዓለም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ደም ተጠምቃ አየችው። ዓለም በነብይነትዎ ዛሬም ይገረማል።

#ንጉሥ ሆይ የነዋይ ወንድማማቾች መፈንቅለ መንግስት የመንግስትዎ ማሻሻያ ምልክት ነበር። እዚህ ላይ ግን ነብይ አለመሆንዎ ቅር ያሰኛል።

ጃንሆይ

እንኳን በታሪካችን መስመር ላይ ያለፉ እንላለን። ልደትዎን እያከበርን መልካም ልደት ብለናል!
146850cookie-check#ክብር ለታላቁ ንጉሥ ልደት ቀን!”ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሡ!” ይልዎ የነበረው ሕዝብ ምን አይቶ ምን ሰ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE