ዳኞች የነገ የፋና ላምሮት ጉዟቸው ላይ በጥንቃቄ እንዲጓዙ መከሩhttps://telegra.ph/file/15b8…

Reading Time: 2 minutes
ዳኞች የነገ የፋና ላምሮት ጉዟቸው ላይ በጥንቃቄ እንዲጓዙ መከሩ

https://telegra.ph/file/15b8c6049718c1b708a07.jpg

ፋና ላምሮት 17 ምዕራፍ የሁለተኛው ምድብ አምስት ተወዳዳሪዎችን በስምነተኛ ሳምንት ከዛየን ባንድ ጋር ሆነው የሙዚቃ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡

*ምን አዲስ ነገር አለ

-ዛየን ባንድ እንደ ተለመደው ወደ 10 የሚጠጉ ሙዚቃዎች ከ ተወዳዳሪዎች ጋር አቅርበዋል፡፡

– እስካሁን በተጓዝንባቸው ሳምንታቶች በዚህ ምዕራፍ አስር ሺህ ነጥብ ተሰቶ አልታወቀም ነበር በቅዳሜው እለት በስምንተኛ ሳምንት ለ አብርሀም ማርልኝ ሙሉ አስርሺህ ነጥብ፡( በወንድሙ ጅራ ሙዚቃ ውቢት) ውቢት ሙዚቃ ኦርጅራል የሙሉቀን መለሰ ተሰቶታል፡፡

– በቀጣይ ሳምንት የሁለቱ ምድብ ተወዳዳሪዎች በአንድ ሆነው አጠቃላይ ስምንት ሆነው ውድድራቸውን ያከናውናሉ፡፡

– አሁን ላይ ከ አስራ ስድስት ተወዳዳሪዎች ውድድሩ ሲጀምር ቆይተው ነበር በዚህም ስድስት ተወዳዳሪዎች እንስካሁንዋ ውድድር ተሰናብተዋል ወደ ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ፍልሚያውስጥ ይገኛሉ፡፡

– ተመልካቶች እንደ ተለመደው በቦታው በመገኘት ውድድሩን በቀጥታ ተከታትለዋል፡፡

* ዳኞች ከስልትም ከስሜትም ሐሳብ ሰተዋል፡፡

-የማይክ አጠቃቀም ፣ ዳናሚክስ ፣ የሙዚቃ አቀራረብ ፣ የሙዚቃ ስሜት መጠበቅ ፣ በራስ ድምፅ ማዜም እና በራስ የሙዚቃ መንገድ ማቅረብ ፣ አይደንቲቲ(ራስን መሆን) ፣ ፍሬዚንግ(የዜማ ሐረጋት) ፣ የዜማ ምርጫ ፣ የሙዚቃ ምርጫ ፣ የድምፅ ጉልበት ምጠና እና አጠቃቀም ፣ የራስ አቅም ፣ የሙዚቃ ሂደቱን ለውጡን ፣ key(ኪ )ምጠና፣  ውበት ቀናሽ የሆነ አቀራረብ ማስወገድ ፣ በራስ ቃና ማቅረብ ፣ሬንጅ ፣ ቫልዩ አድ (አዲስ ነገር ማቅረብ) ፣ በራስ መተማመን እና የመሳሰሉ አስተያየት ተሰቷል፡፡

* ዛየን ባንድ አስር ሙዚቃዎችን ከተወዳዳሪዎች ጋር ሆነው አቅርበዋል፡፡

ማዲንጎ አፈወርቅ ( አንቺ ቆንጆ) ፣ የወንድሙ ጅራ(ውቢት) ኦርጂናሉ ሙዚቃ የሙሉቀን መለሰ ፣ ሚሊክ ወስናቸው( ፍቅር በአስተርጓሚ)፣ ተፈራ ነጋሽ(ተመለሽ) ፣ ግርማ ተፈራ( ታድያለሁ) ፣ ጋሽ ጥላሁን ገሰሰ(ሸሙና) እና የመሳሰሉት በመድረኩ ቀርበዋል፡፡

* ዳኞች ለሕይወታችን ስንቅ ለተወዳዳሪዎች ብርታት ሰተዋል፡፡

-የሹምነሽ ታዬ:- የምንመርጠው ሙዚቃ ለድምፃችን ተስማሚ እና ለድምፃችን ከለር የሚሆነን መምረጥ አለብን፡፡

-አማኑኤል ይልማ:- በሙዚቃ ውስጥ ሁሌም ልምምድ ልምምድ ማድረግ አለብን ፡፡

– ብሩክ አሰፋ :- በፋና ላምሮት ቤት የትኛዋም ቅዳሜ የፍፃሜን ያህል ይቆጠራል፡፡

*ያለፉ ተወዳዳሪዎች እና የተሰናባቹን ሙሉ ነጥብ እንግለፅላችሁ፡፡

-አብርሀም ማርልኝ:- 59520 አጠቃላይ ነጥብ፡፡
-ሱራፌል ደረጄ-58956 አጠቃላይ ነጥብ፡፡
-ሄኖክ ዓለሙ-58867 አጠቃላይ ነጥብ ፡፡
-ጌታሁን ተረፈ-58805 አጠቃላይ ነጥብ፡፡
-ቢኒያም ዘውዱ -58163 አጠቃላይ ውጤት

ቢኒያም ዘውዱ”ማመስገን ምፈልጋቸው ሰዎች አሉ ቤተሰቦቼን ባለቤቴ ሄሮና እንደ ምታስቡት ባልሄድም ነገም እንቀጥላለን ብዬ አስባለሁ ዳኖችን የሞያ አጋሮቼ ሁሉንም አመሰግናለሁ” ፍና ላምሮት ከ 8000 ብር ጋር አብሮነቱን ገልፆ አሰናብቶታል፡፡

ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
ፋና ላምሮት
yenevibe.com ጎብኙን እናመሰግናለን
145710cookie-checkዳኞች የነገ የፋና ላምሮት ጉዟቸው ላይ በጥንቃቄ እንዲጓዙ መከሩhttps://telegra.ph/file/15b8…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE