የወባ ወረርሽኝ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ለሚዲያ ባለሙያዎች ተሰጠ።
የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል እየተወሰዱ የሚገኙ ስትራቴጂዎችን ለሚዲያ ባለሙያዎቹ ያብራሩት በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ ሲሆኑ፤ ኢንስቲትዩቱ ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በቅርበት በመስራት ወቅታዊ መረጃዎችን እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
የወባ ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚደረገው ሃገራዊ ጥረት ከሚዲያ ተቋማት ምን እንደሚጠበቅ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀው ስልጠና በኮቪድ ወረርሽኝ መከላከል በሚዲያ ፎረሙ የተገኙ ውጤቶችን እና ተሞክሮዎችን በወባ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ለመድገም እንዲቻል ለማመቻቸት የተዘጋጀ ስለጠና መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ የገለጹ ሲሆን፤ ህብረተሰቡን ከወባ ለመከላከል ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ ለህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ማድረስ በመሆኑ ስልጠናውን መሰጠት ማስፈለጉን አስረድተዋል፡፡
ወቅቱ የክረምት ወቅት እንደመሆኑ መጠን ከወባ በሽታ በተጨማሪ ህብረተሰቡ ከሌሎች ዉሃ ወለድ በሽታዎች ራሱን እንዲጠብቅ የሚዲያ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በተከታታይነት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት በስልጠናው ለተሳተፉ የሚዲያ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ አሁናዊ የወባ በሽታ ስርጭት ሪፖርት የኢትዮጵያ ብሄራዊ የወባ መቆጣጠሪያ ፕሮግራም ገለጻ የቀረበላቸው ሲሆን፤ ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡