ስቅ አለኝ አልበም ወርሀዊ የአልበም ትውስታ …
በወርሀዊ የሙዚቃ አልበም የምናመሰግነው የድምፃዊ ሽዋንዳኝ ሀይሉ የመጀመርያ አልበም ”ስቅ አለኝ” ይሆናል፡፡ አልበሙ 1996 የወጣ አልበም በቮይስ ሙዚቃ ቤት የታተመ ሲሆን በውስጡ አስራአንድ (11) የሙዚቃ ክሮች ሲኖሩት ጥርስሽ ለይምሰል ፣ አኩኩሉ ነጋ ወይ ሌቱ ፣ እያት ይለኛል ፣ ዐይኔ ፣ የአልበሙ መጠርያ ስቅ አለኝን ጨምሮ ይገኙበታል ፡፡
በዚህ አልበም ብዙ ስሜቱችን ድምፃዊው ለማጋራት ሞክሯል ክህደትን ፣ ምኞትን ፣ የፍቅርን ጥግን ፣ ትዝታን ከ ምስለ ክሰታ ጋር ፣ የመጀነን ወይም የኩራት ስሜት ፣ ከራስ አልፎ በፍቅር ሰው መናፈቅ ፣ ስለ ውበት ፣ የመሳሰሉት አሉበት፡፡
ታላላቅ ከያኒያን ተሳትፈዋል በግጥም በዜማ ዳዊት ፅጌ( አክሱማዊት ባንድ) ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን ( ቴዲ አፍሮ) ፣ ግርማ በየነ ናቸው በቅንብሩ ግሩም መዝሙር ፣ አበጋዝ ክብረወርቅ እና አፍሮ ሳውንድ ባንድ ተሳትፈዋል፡፡
* ጥርስሽ ለይምሰል…
“እንደ ምወድሽ ልብሽ ያውቀዋል
ጥርስሽ ለይምሰል ምን ያስቀዋል
አታሳዝኝው በአጉል ፈገግታ
ይቆርጣል ልቤ ያዘነ ለታ“…
ግጥም ዳዊት ፅጌ( የአክሱማዊት ባንድ ባለቤት) ዜማ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ቅንብር ግሩም መዝሙር:: ልብሽ ለምን አይረዳኝም እኔ የእውነቴን ነው ከቀልድ አትውስጂው ሲል የሚማፀንበት ነው፡፡
* ታምራለች…
በሰንበት ከመቅደስ ባገቢስ ምን አለ?
ዞረው አዩሽ ቄሱ ቅዳሴ ታሎለ
አሳምሮ ሰርቶሽ
ለፈተና አረገሽ ታምራለች …
ግጥም እና ዜማ ቴዎድሮስ ካሁን ( ቴዲ አፍሮ) ቅንብር ግሩም መዝሙር ፡፡
የውበትን ጥግ ማሳያ በለተያዩ አገላለፅ የገለፀበት ማፍቀር ከውበት ጋር ይለካል ይህም ሙዚቃ ከውበት እና ከአድናቆት ጋር ገልጿታል፡፡
ፅጌሬዳ…
“አርጓዴ አይደለም ነጭ አትመስል ቢጫ
መለየም አቃተኝ የቀልምዋን ምርጫ
ብቅ ብላ ላያት ፈክታ በማለዳ
ደስ ትለኛለች የእኔ ፅጌሬዳ”…
ግጥም እና ዜማ ግርማ በየነ ቅንብር አፍሮ ሳውንድ ባንድ ይህ ሙዚቃ ኦርጅናሉ የግርማ በየነ ሙዚቃ ነው፡፡
ውበት እንደ ተመልካቹ በተለያየ መንገድ ይገልፀዋል አንዲት ማራኪ ሴትን በፅጌሬዳ መስሏት ውበትዋን በሷ ውስጥ ይገልፃል መሸነፍን ፣ ማፍቀርን ፣ ማክበርን በሙዚቃ ውስጥ ይንፀባረቃሉ፡፡
ስቅ አለኝ አልበም በርካታ ጉዳዮችን አዝሎ ዘመን ከ ዘመን እንደ አዲስ ይደመጣል የኔ ቫይብ ወርሀዊ የሙዚቃ አልበም ምርጫ ይንን መረጥን አድምጡት እናመሰግናለን፡፡
yenevibe.com ይጎብኙ እናመሰግናለን