አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች እንዲሁም በሙዚቃ ሳምንታዊ ጉዳይ በየሳምንቱ የምንጋብዛችሁ አልበም እንደ ተጠበቀ ነ…

Reading Time: 3 minutes
አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች እንዲሁም በሙዚቃ ሳምንታዊ ጉዳይ በየሳምንቱ የምንጋብዛችሁ አልበም እንደ ተጠበቀ ነው፡፡-ዝናሽ ውቤ- ”ልትናፍቀኝ ነው” ከረዥም ጊዜ በኃላ በአዲስ ነጠላ ሙዚቃ መጣለች ግጥሙን እዮኤል ብርሀኑ ዜማ ዘላለም ተረፈ ቅንብር ኤርሚያስ በዳዳ በቅርቡ በናሆም ሪከርድስ በኩል ለ አድማጭ ይደርሳል ተብሏል፡፡– ዳዊት ፅጌ-  ወደ አሜሪካ ተጎዞ የሙዚቃ ስራውን በአትላታ july 05/2024 ለማቅረብ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡ ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ከ የኔ ዜማ ባንድ ጋር ሙሉ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ እና ከምነው ሸዋ ኢንተርቴመንት ጋር በመተባበር ወደ አሜሪካ ተጉዘው የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ሊያቀርቡ መሆኑንም ገልጿል፡፡-ማስተዋል እያዩ -”እመጣለሁ” ሁለተኛ ቪድዮ ስራ ከአዲሱ የበኩር አልበሙ ”እንዚራ”ስር የሚገኘሁ መጣለሁ የተሰኘውን ስራ በምስል ሰርቶ ወደ ህዝብ ሊያሻግር ነው ይህ ሙዚቃ ግጥም እና ዜማ አብዲ ሲሰራው ቅንብር እና ሚክስ ሚካኤል ሀይሉ ማስተሪንግ ሰለሞን ሀይለማርያም፡፡-አብዚ ሰሙን እና ዳዊት ገ/ስላሴ-ካቢላ -“ሸጋ” የተሰኘ አብረው በጋራ ይዘውልን እየመጡ ይገኛሉ  ግጥም እና ዜማ ዳዊት ገ/ስላሴ-ካቢሊ ሲሰራው ቅንብሩን አስፋ አበበ ሰርቶታል፡፡-ሳሙኤል ብርሀኑ “ሳሚ ዳን”-“ካለሽ አንቺ” የተሰኘ ከዚህ ቀደም የተሰራ ሙዚቃ በአዲሱ እስቱዲዮ ሮፍቶፕ  እንደገና በላይቭ ሚውዚክ የተሰራውን ያደርሰናል ግጥም ዜማ ሳሚ ዳን ቅንብር ኤንዲ ቤተ ዜማ፡፡-ራፐር ወዲ ሃይለ ”ሃርኳት” የተሰኘ ሙዚቃ ከሰሙኑ ወደ አድማጭ ደርሶ ነበር ግጥሙን ተስፋይ አምሳ ዜማ ይርግሻ ቅንብር ተሴ ዋካ ናቸውጎልደን ፕሮዳክሽን በኩል ተለቋል ገብታችሁ መመልከብ ትችላላችሁ፡፡– ጋዜጠኛ መሰለ ገ/ሕይወት ” መሼ ሾው” የተሰኘ አዝናኝ ፕሮግራም ይዞ እየመጣ ይገኛል በዜና አንባቢነት የምናውቀው ጋዜጠኛ መሰለ ገ/ ሕይወት የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 29/2016 በዓባይ ቲቪ ምሽት ላይ በውስጡ የተለያዩ መሰናዶዎችን ተካትተው ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡-“ኦሎምፒክ ኮንሰርት በ መስቀል አደባባይ” ሐምሌ 9/2016 ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል በዚህ ኮንሰርት ላይ የሚሳተፉ ድምፃዊያን መካከል ንዋይ ደበበ ፣ ሸዋንዳኝ ኃይሉ ፣ዳዊት መለሰ ፣ አንድዋለም ጎሳ ፣ ሔለን በረሔ እና የመሳሰሉት በዝግጅት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መግቢያ 500 ብር፡፡– ሚዲያ ሐዋርድ -የመጀመርያ ሚዲያ አዋርድ ሊዘጋጅ መሆኑን ተገልጿል፡፡ ሚዲያ አዋርዱ በቲቪ ፡ በሬድዮ እና በጋዜጣ ባለሞያዎች ጋዜጠኞችን 18 ዘርፎች ቀርቦ ውድድሩ ይከናወናል ተብሏል፡፡ ባለፈው አመት ሴኔ ወር ጀምሮ የተላለፉ ፕሮግራሞች እና ለሰባት ወራት ስራ ላይ የነበሩ የሚዲያ ባለሞያዎች ለ እጩነት ቀርቧል፡፡ ለታጫችሁ የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት  መልካም እድል ይመኝላችኃል፡፡

* የአልበም ምረቃ እና የሚወጡ የአልበም ጥቆማ– የድምፃዊት ለምለም ኃ/ማርያም ባሳለፈነው ግንቦት 9/2016 የበኩር አልበምዋ ” ማያዬ” መውጣቱ አይዘነጋም አሁን ደሞ የአልበሙ ምርቃት የፊታችን ሰኔ 22/2016 በማርዮት ሆቴል ይከናወናል፡፡በዝግጅቱም ግርማ ተፈራ ፣ ጌታቸው ተሾመ ፣ ኤደን አይሸሹም የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡– አዲስ አለማየሁ( አዲንቆ) –  አዲስ የመጀመርያ የሙዚቃ አልበም ሊለቅ ነው፡፡ አዲስ አለማየሁ በማሲንቆ የታጀበ ጣዕመ የሙዚቃ በአዲስ አደራረብ በቅርቡ ወደ እናንተ ይደርሳል ብሏል፡፡– አብዱ ኪያር አምስተኛ አልበሙን ”ፓ ፓ ፓ” የተሰኘው የፊታችን አርብ 22/2016  በራሱ ዩትዮብ ቻናል አብዱ ኪያር ይለቀቃል፡፡በአምስተኛ አልበሙ ላይ በርካታ የሙዚቃ ባለሞያዎች ተሳትፈዋል በቅንብር ስማገኘሁ ሳሙኤል ፣ ኪሩቤል ተስፋዬ ፣ ካሙዙ ካሳ እና ዳዊት ቦስኮ ተሳትፈዋል፡፡ በሙዚቃ መሳርያ ሮቤል መሖሪ ፣ ሉዋም መሀሪ ፣ ዘሪሁን በለጠ ፣ ታመነ መኮንን ፣ ደግሰው አበበ እና ጉልላት ፡፡ በአጃቢነት ሳሙኤል አድማሱ እና ረድኤት ሙሉጌታ ሚክሲንግ ስማገኘሁ ሳሙኤል እና ኪሩቤል ተስፋዬ በማስተሪንጉ አበጋዝ ክብረወርቅ ሽኦታ ናቸው ፡፡ አቡዲ ኪያር ከዚህ ቀደም መርካቶ ሰፈሬ ፣ ፍቅር በአማርኛ ፣ ምነው ሸዋ ፣ ጥቁር አንበሳ አልበሞችን ለህዝብ ማድረሱ አይዘነጋም፡፡

* በዚህ ሳምንት ሙዚቃዊ ጉዳይ ከተሰሙት ውስጥ…-በሸራተን አዲስ ሰኔ 15/2016 አመተ ምህረት ሶስት ድምፃዊያንን አጣምሮ”Eleganeኮንሰርት” ባሳለፍነው ሳምንት ተከናውኖ ነበር ፡፡እነዚህ ሶስቱ ድምፃዊያን አብርሀም ገብረ መድህን ፣ ጌታቸው ሐይለማርም በተጨማሪም ዳዊት መለሰ ተጣምረው የሙዚቃ ዝግጅታቸውን አቅርበዋል፡፡– የኢትዮጲያ አይደል ሶስተኛ ምዕራፍ በደማቅ ሁኔታ ያጠናቀቀበት ሳምንት ነበር፡፡ በሶስተኛው ምዕራፍ የባለ ተስዕጦ ውድድር አንድ ሚልየን ብር እና የክብር ዋንጫ ወስደዋል በድምፅ ድምፃዊት መብራት ንጉሴ በተውኔቱ ተዋናይ መድሐኒት ዘገየ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡– የሙዚቃ ባለሞያ የግጥም ዜማ ደራሲ ፣ አቀናባሪ እንዲሁም ዳይሬክተር አብርሀም ወልዴ ባሳለፍነው ሳምንት የጊፍት ሪል ስቴት ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመርጧል፡፡ አርቲስት አብርሀም ወልዴ የባላገሩ አይደል ዳኛ ሆኖ በርካቶችን አዳዲስ ድምፃዊያ ከአረጋኸን ወራሽ እና ከሱልጣን ኑሪ ጋር አብሮ በመሆን ወደ ኢንደስትሪው ቀላቅሏል፡፡

* የኔ ቫይብ በዚህ ሳምንት የመረጥንላችሁ አልበም…

የድምፃዊ አብነት አጎናፍር የመጀመርያ አልበም ”ድብቅ ውበት” ይህ አልበም በበርካቶች ሰዎች ስር ታትሞ የቆየ እና  ትልቅ ትዝታን ያዘለ ነው በውስጡ 13 የሙዚቃ ክር ሲኖረው አብዛኛውን ግጥም እና በዜማ አብነት አጎናፍር ሲሰራው የአብነት አጎናፍር ወንድም  ፍፁም ካሳሁን በዜማ አግዞታል፡፡በቅንብር እና ሚክስ እና ማስተሪንግ ኤልያስ መልካ በቅንብር ድምፃዊ አብነት አጎናፍ ፡፡ በድምፅ እጀባ አብነት አጎናፍር ፣ ቤዝ ጊታሪስት ኤፍሬም አስራት እና ኤልያስ መልካ ናቸው ኤክስኪውቲቪ ብሮዲውሰር መታሰብያ ዘውዴ፡፡

@biggrs yenevibe.com ጎብኙን እናመሰግናለን፡፡
142100cookie-checkአዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች እንዲሁም በሙዚቃ ሳምንታዊ ጉዳይ በየሳምንቱ የምንጋብዛችሁ አልበም እንደ ተጠበቀ ነ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE