በዚህኛው ዙር የጥናት ጉድለት እንዳለባቸው ዳኞች ገልፀዋል፡፡https://telegra.ph/file/a85831…

Reading Time: 2 minutes
በዚህኛው ዙር የጥናት ጉድለት እንዳለባቸው ዳኞች ገልፀዋል፡፡



ፋና ላምሮት ስድስተኛ ሳምንት ስድስት ተወዳዳሪዎችን ይዞ ከዛይን ባንድ ጋር እንደ ወትሮ ሁሉ ድምቅ አርገው አቅርበዋል፡፡ ፋና ላምሮት 16 ተወዳዳሪዎች ይዞ የጀመረው እና በአስራ ሶስተኛ ሳምንት አራት ምርጦች ይዞ ፍፃሜውን ያደርጋል፡፡



* አዲስ ነገር ምን አለ፡፡



– ተወዳዳሪዎች የመጀመርያ ዙር በራሳቸው በመረጡት ሙዚቃ አወዳድረው በሁለተኛ ዙር ደሞ ዳኞች በመረጡላቸው ሙዚቃዎች ተወዳድረዋል ዳኞች የመረጡላቸው ሙዚቃዎች የሴቱንም የወንዱንም ሁሉም ሙዚቃዎች ሴቱም ወንዱም ተወዳዳሪ መዝፈን ይችላሉ፡፡



– ተመልካቾች በቦታው በመገኘት የተወዳዳሪ ቤተሰብ  ፣የሙዚቃ አፍቃሪያን፣ ተወዳዳሪዎች የሚናፍቁ ሰዎች በቦታው በመገኘት ውድድሩን አይተዋል፡፡



-በውድድሩ የግጥም ከዜማ ከቅንብር የተሰሩትን ሙዚቃዎች ይልማ ገብረአብ፣ ጌታቸው ደባልቄ ፣ ካሳ ወልዴ ፣ አለምፀሐይ ወዳጆ ፣ አየለ ማሞ ከ ቅንብር ኤልያስ መልካ ፣ አበጋዝ ፣ ክብሩዘበኛዎች ፣ ውሴ መርሲ እና የመሳሰሉት ቀርበዋል፡፡



* ዛይን ባንዶች ከ ተወዳዳሪዎች ጋር ሆነው 12 ሙዚቃዎችን ተጫውተዋል፡፡



– ንዋይ ደበበ/ተውኝ/ ፣ በዛወልቅ አስፋው/ወዳጅ ያጣ ጎጆ/ ፣ ሙሉቀን መለሰ/ ቁመትሽ ሎጋ ነው/ ፣ ጥላሁንን  ገሰሰ/ የግሌ ነሽ/ ፣  ግርማ ነጋሽ/ የኔ ሀሳብ / ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ/ሸጋ ልጅ/ ፣ ገረመው አሰፋ/ጭር አለ/ ፣ ማስተዋል እያዩ/ መጥቼ ነበር/ የመሳሰሉት አሉት፡፡



* ዳኞች ከስልትም ከስሜትም አስተያየት ሰተዋል፡፡



…ትኩረት ሰቶ መስራት ፣ የሙዚቃ ምርጫ ፣ የቃላት አጠቃቀም ፣ ኦርናመንት ፣ ለጆሮ በሚጥም መልኩ ማቅረብ ፣ ወደራስ ድምፅ መምጣት  ፣ ለውጥ ፣ ቴንፖ ፣ አገላለፅ ፣ ቅኝት ፣  ቫልዩ አድ ፣ ጉልበት ምጠና እና አጠቃቀም፣ ዳናሚክስ ፣ ናዛል ቮይስ ፣ እርታ ፣ ጥሞና ፣ ዜማ እጥፋት ፣ በሌላ አይነት የተሰራ ሙዚቃ መልሶ መስራት  ፣ የማይክ አጠቃቀም እና የመሳሰሉት ቀርበዋል፡፡

* ዳኞች ለሕይወታችን ስንቅ እና ለተወዳዳሪዎች ብርታት ሰተዋል፡፡



– የሹምነሽ ታዬ :- ኦርጅናል የሆነውን ስራ ወደ ራስ  ወስዶ  ማቅረብ አለባችሁ፡፡

-ብሩክ አሰፋ :-ልክ ሙዚቃው ሲጀመር በትኩረት መጀመር አለብን፡፡



– አማኑኤል ይልማ :- በምታቀርቡት ሙዚቃ እጅጉኑ ተዘጋጅታችሁ ጥናት አድርጋችሁ ቅረቡ ያለዛ እየወደድናችሁ እንሸኛቹኃለን፡፡



ያለፉ እና የተሰናባቹን ሙሉ ነጥብ እናደርሳቹኃለን፡፡

– አብርሀም ማርልኝ-59120 አጠቃላይ ነጥብ፡፡
– ሱራፌል ደረጄ-58868 አጠቃላይ ነጥብ፡፡
– ቢንያም ዘውዱ – 58749 አጠቃላይ ነጥብ፡፡
– ሄኖክ አለሙ-58620 አጠቃላይ ነጥብ ፡፡

– የእለቱ ተሰናባች በዳኞች አስተያየት ረዥም ጉዞ እንደምትሄድ ተስፋ ተጥሎባት ነበር::  ደስ የሚል ሽክር ያለ የሚወደድ ድምፅ ያላት መሆኗን ዳኞች መስክረዋል በስተመጨረሻም የጥናት ጉድረት ከውድድሩ ልትሰናበት ችላለች ፡፡

– ስንታየሁ በላይ-” የጥናት ችግር አጋጥሞኝ ነበር ግን ከልብ አመሰግናለሁ”” ገልፃለች፡፡



ስንታየሁ በላይ – 58050 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት ፋና ላምሮት አብሮነቱን ገልፆ ከ 7000 ብር ጋር በፍቅር ሸኝቷቷል፡፡


ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
ፋና ላምሮት ፡፡




yenevibe.com ስለ ምትጎበኙን እናመሰግናለን፡፡
141920cookie-checkበዚህኛው ዙር የጥናት ጉድለት እንዳለባቸው ዳኞች ገልፀዋል፡፡https://telegra.ph/file/a85831…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE