“ሜላድ የብራና ማዕድ” አውደ ርዕይ ተከፈተ።
ሜላድ ጥንታዊ የብራና ጽሁፍ መጻፊያ ፣ የስዕል መሳያ እና ማሰልጠኛ ማዕከል “ኑ ! ድንቅ ነገር እዩ !” በሚል መሪ ሀሳብ ሰኔ 8 እና 9 ቀን 2016ዓ.ም በቦሌ መድኅኔዓለም ካቴደራል ብፅዕ አብነ ኤፍሬም ፣ ብፅዕ አብነ ሠላማ ፣ ብፅዕ አብነ እስጢፋኖስ ፣ የጥበብ ባለሙያዎች እና ምዕመናን በተገኙበት ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓም ተከፈተ።
ሜላድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዝግጅት ማእከል በደብረ ሊባኖሱ የሃይማኖት፣ የቅርስ፣ የታሪክ ፣ የስርዓተ ቤክርስቲያን ተቆርቋሪ በሆኑት በቆሞስ አባ ኪዳነ ማርያም አበበ እና በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው አማካኝነት የተቋቋመ ማእከል ነው።
ሜላድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዝግጅት ማእከል የብራና ቆዳዎች ዝግጅትን ጨምሮ፣ የብራና ጽሑፍ እርማት ፣ ድጉሰት ፣ የቅዱሳን ሥዕላት አሣሣልና የሐረግ አሠራር ሙያዎችን በአንድ ማእከል ሥር በማደራጀት እና ለዚህ ስራ የሚሆኑ የቅኔና የመጻሕፍት መምህራንና ሠራተኞችን በመቅጠር ሥራዎችን የጀመረ ሲሆን ፤ የተለያዩ ገድላት ፣ ድርሳናት ፣ መልኮችና ተአምራት እንዲሁም አነስተኛ የጸሎት መጻሕፍት በዚሁ ድርጅት ተዘጋጅተው ወደ ተለያዩ ገዳማትና አድባራት ተሰራጭተው አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በተለያዬ የእድሜ እና የዕውቀት ደረጃ ላይ ለሚገኙ አገልጋዩችና ምእመናን ሥልጠናዎችን በመስጠት በርካታ ንቁና የተማሩ ሰዎችን ማፍራት ተችሏል፡፡
ኹነቱን ያዘጋጀው መንፈሳዊ መርሐግብሮች በማዘጋጀት ከፍተኛ ልምድ ያለው ሎዛ ኹነቶች ነው።
ሜላድ ጥንታዊ የብራና ጽሁፍ መጻፊያ ፣ የስዕል መሳያ እና ማሰልጠኛ ማዕከል “ኑ ! ድንቅ ነገር እዩ !” በሚል መሪ ሀሳብ ሰኔ 8 እና 9 ቀን 2016ዓ.ም በቦሌ መድኅኔዓለም ካቴደራል ብፅዕ አብነ ኤፍሬም ፣ ብፅዕ አብነ ሠላማ ፣ ብፅዕ አብነ እስጢፋኖስ ፣ የጥበብ ባለሙያዎች እና ምዕመናን በተገኙበት ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓም ተከፈተ።
ሜላድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዝግጅት ማእከል በደብረ ሊባኖሱ የሃይማኖት፣ የቅርስ፣ የታሪክ ፣ የስርዓተ ቤክርስቲያን ተቆርቋሪ በሆኑት በቆሞስ አባ ኪዳነ ማርያም አበበ እና በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው አማካኝነት የተቋቋመ ማእከል ነው።
ሜላድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዝግጅት ማእከል የብራና ቆዳዎች ዝግጅትን ጨምሮ፣ የብራና ጽሑፍ እርማት ፣ ድጉሰት ፣ የቅዱሳን ሥዕላት አሣሣልና የሐረግ አሠራር ሙያዎችን በአንድ ማእከል ሥር በማደራጀት እና ለዚህ ስራ የሚሆኑ የቅኔና የመጻሕፍት መምህራንና ሠራተኞችን በመቅጠር ሥራዎችን የጀመረ ሲሆን ፤ የተለያዩ ገድላት ፣ ድርሳናት ፣ መልኮችና ተአምራት እንዲሁም አነስተኛ የጸሎት መጻሕፍት በዚሁ ድርጅት ተዘጋጅተው ወደ ተለያዩ ገዳማትና አድባራት ተሰራጭተው አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡
- See also: ዜና ዕረፍት የድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ…