ድምፃዊት እና የደሞ አዲስ የባለተስዖጦ ውድድር ዳኛ ትዕግስት ሀይሉ ( እግቱ) አሳዛኝ ክስተት እንደገጠማት …

Reading Time: < 1 minute
ድምፃዊት እና የደሞ አዲስ የባለተስዖጦ ውድድር ዳኛ ትዕግስት ሀይሉ ( እግቱ) አሳዛኝ ክስተት እንደገጠማት ተገለፀ፡፡



…በትናትናው እለት በ21/2016 የሜትር ታክሲ አሽከርካሪ የመደፈር ጥቃት እንደደረሰባት ድምፃዊት ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) ገልፃለች።

እንዲህ ስትል በፅሁፍ አስረድታለች “ትላንትና በከተማችን የሚሰራ የሜትር ታክሲ ሹፌር ሊደፍረኝ ነበረ ያለችው ድምፃዊቷ ከቤት ስወጣ ያደረሰኝን ሹፌር አመሻለሁ ሲለኝ ፕሮግራሜን ስጨርስ ቤቴን ስለሚያውቀውም መጀመሪያ በሰላም ስላደረሰኝም ወደ ቤት እንዲመልሰኝ ደወልኩለት ትንሽ ቢያረፍድም መጣ ስትል የተፈጠረውን አብራርታለች።



ቤት ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ መኪናውን አቁሞ ሲታገለኝ እወጋሻለሁ ብሎ ሲያስፈራራኝ፣ አምልጬ ወደ ቤት ገብቻለሁ። ሲታገለኝ ልብሴ ስለተቀደደ ኪሴ ውስጥ የነበረ ገንዘብ ሙሉበሙሉ መኪና ውስጥ ወድቆብኛል” ብላለች።



ትማሩበታላችሁ፣ የእኔን ስህተት ተዘናግታችሁ አትደግሙትም ብዬ አምናለሁ ስትል እግቱ የደረሰባትን ገልፃለች።

መረጃው ትንሽ ዘግይት ቢልም ግን እንድትማሩበት እና ጥንቃቄያችሁ ምን ግዜም አይለይ፡፡
138240cookie-checkድምፃዊት እና የደሞ አዲስ የባለተስዖጦ ውድድር ዳኛ ትዕግስት ሀይሉ ( እግቱ) አሳዛኝ ክስተት እንደገጠማት …

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE