አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎችን እና ሙዚቃዊ ጉዳይ በተጨማሪም በየሳምንት የመጥላችሁ የአልበም ግብዣ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፡፡
-ድምፃዊ ካሳሁን እሸቱ (ካሳሁን) አርብ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም በሀዋሳ “ሳውዝ ስታርኢንተርናሽናል ሆቴል”በድምቀት ይመረቃል።በቴድኔት ኢንተርቴይመንትና በኪነት ኢንተርቴይመንት አዘጋጅነት በድምቀት በሀዋሳ ይመረቃል፡፡ከዚህ ቀደም በሸራተን አዲስ እና በአርባምንጭ አልበሙን ማስመረቁ ይታወሳል፡፡
– በዋልታ ቲቪ ዘውትር እሁድ ከ ቀኑ 9:00 /ዘጠኝ ሰዓት/ የሚተላለፈው “ደሞ አዲስ” የባለ ተስዕጦ የድምፃዊያን ውድድር ግንቦት 25/ 2016 የመጀመርያ ምዕራፉን ፍፃሜን ያገኛል ተብሏል፡፡ የዳኞች እና ተወዳዳሪዎች ያሬድ ነጉ ፣ የሺህ ደንበላሽ ፣ ትዕግስት ሀይሉ( እግቱ) በቦታው ተሰይመው ይዳኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
– በአባይ ቲቪ አዳዲስ እና ምርጥ ፕሮግራሞችን ይዞ እየመጡ ይገኛሉ፡፡ ከዛ ውስጥ ታዋቂ የዜና አንባቢ ጋዜጠኛ መለሰ ገብረ ሕይወት ከዜና አባቢነት ወደ መዝናኛው ዘርፍ በመቀላቀል”መሴ ሾው” የተሰኘ ፕሮግራም ይዞ እየመጣ ይገኛል አርቲስት ሜላት ነብዩ “ሀባይ ሄሎ” ራኬብ አለማየሁ” በዚህ ሳምንት ራኪ” ሌሎችም ዝግጅታቸውን አሰናድተው በቅርብ በአባይ ቲቪ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
– በቅርብ ቀን የ”ሚዲያ አዋርድ” እንደሚካሄድ እየተገለፀ ይገኛል፡፡ የተለያዩ በሚዲያ ዘርፍ መሸለም የሚገባቸው ሚዲያ አካላት የተለያዩ የሚዲያ ከዋኞች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
* ሙዚቃዊ ክስተት በዚህ ሳምንት እናንሳ
-ተወዳጁ የፋና ላምሮት ተወዳዳሪ ሐብታሙ ይሄ ነው ”የመቶ ሺህ ብርሽልማት እና የ200መቶ ካሬ መሬት ተብርክቶለታል”በፋና ላምሮት አራተኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ አራተኛ በመውጣት ህዝብን አስደምሞ ነበር፡፡ ድምፃዊ አብታሙ ይሄነው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በፍኖተ ሰላም ከተማ ደማቅ አቀባበል እንደ ተደረገለት ሰምተናል።በየፍኖተ ሰላም ከተማ የጃቢ ጠህናን አስተዳደር ምክርቤት “የ100 ሽህ”ብር እና “በማንኩሳ” ከተማ የ200 ካሬ ሜትር ቦታ ተበርክቶለታል፡፡
– 13ኛው ለዛ አዋርድ ግንቦት16/2016 ታላላቅ የኪነጥበብ ሰዎች በተገኙበት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ዝግጅቱ ተከናውኗል፡፡ በዚህ የለዛ ሽልማት አርቲስት መስከረም አበራ እና “በስንቱ” ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከ አንድ በላይ ሽልማቶችን ወስደዋል፡፡ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ” ንዋይ ደበበ” ሆኖ ተመርጧል፡፡
ተዋናይት መስከረም አበራ
-የዓይን አፋርዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ግንቦት 9/ 2016 “አንፀባራቂዋ ኮከብ ” መፅሐፍ የተመረቀበት ሳምንት ነበር ፡፡ የድምፃዊት ሂሩት በቀለ የሙዚቃ ጉዞ እና የግለ የሕይወት መንገድ የሚያጠነጥን እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት በኢሊሌ ሆቴል ስለ መፅሐፉ እና ስለ ተለያዩ ጉዳዮች ተነስተዋል ፡፡ መፅሐፉ 2.5 ሚልየን ብር እንደ ፈጀበትም ተገልጿል፡፡
– ሶስተኛ ምዕራፍ የNBC ኢትዮጵያ የባለ ተሰጥዖ የድምፃዊያን ውድድርን ከመያዚያ 27/2016 – ግንቦት 17/ 2016 በደማቅ ሁኔታ አስጀምሮ በደመቀ ሁኔታ ጨርሶታል። ለ22 ቀናት የቆየው ውድድሩ 21 አዳዲስ ድምፃዊያንን ያሳተፈ ሲሆን። ልምድ ያላቸው የሙዚቃ ከያኒያን ሁንአንተ ሙሉ፣ ዓለማየሁ ደመቀ፣ እዩኤል መሐሪ እና ድምፃዊ ጌታቸው አስፋው ዳኝነት እየሰጡበት ቆይተውም ነበር።
በመጨረሻም አራት ምርጥ ድምፃዊያን ግንቦት 17/2016 አመሻሽ ከኢትዮ ለዛ ባንድ ጋር ሆነው አወዳድሯል፡፡ ድምፃዊ ዮሐንስ እሸቱ ፣ ራሄል ተሬሳ ፣ ትንቢተ ኢሳያስ ፣ ፣ ብስራት አለማየሁ ፣ ከ አንድ እስከ አራት ጀረጃ ይዘው ጨርሰዋለሁ፡፡
* በዚህ ሳምንት የምንጋብዛችሁ አልበም…
ድምፃዊ የግጥም ዜማ ደራሲ ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ/ ”ሌቦ” የተሰኘ አልበምን ይህ አልበም ሙዚቃ ሲሰራ የመጀመርያ ነበር ሲወጣ ግን ሁለተኛ አልበም ሆኖ ለህዝብ ደርሷል፡፡ ሙሉ በሙሉ ግጥም እና ዜማ ቴዎድሮስ ካሳሁን/ቴዲ አፍሮ/ ቅንብሩን ሙሉ በሙሉ ኤክስፕረስ ባንድ ሰርተውታል፡፡ በውስጡ 11 ትራኮች ሲኖሩ ሌቦ ፣ ዋ ዘንድሮ ፣ትዝብት ፣ ሀገሬ ፣ ጓደኛ እና የመሳሰሉት አሉበት ቴዲ አፍሮ ለሌሎች ዝነኛ ድምፃዊያን የሙዚቃ ስራዎችን ሲሰጥም አስቦ ነበር፡፡
Musics, New Releases, Music Videos
@yenevibe @biggrs የኔ ቫይብ yenevibe.com ጎብኙን