Nbc ኢትዮጲያ የባለ ተስዖጦ የድምፃዊያንን ውድድር ፍፃሜውን አጊኝቷል፡፡ሶስተኛ ምዕራፍ የNBC ኢትዮጵያ የ…

Reading Time: < 1 minute
*
Nbc ኢትዮጲያ የባለ ተስዖጦ የድምፃዊያንን ውድድር ፍፃሜውን አጊኝቷል፡፡

ሶስተኛ ምዕራፍ የNBC ኢትዮጵያ የባለ ተሰጥዖ የድምፃዊያን ውድድርን ከመያዚያ 27/2016 –  ግንቦት 17/ 2016 በደማቅ ሁኔታ አስጀምሮ በደመቀ ሁኔታ ጨርሶታል።

ለ22 ቀናት የቆየው ውድድሩ 21 አዳዲስ ድምፃዊያንን ያሳተፈ ሲሆን። ልምድ ያላቸው የሙዚቃ ከያኒያን ሁንአንተ ሙሉ፣ ዓለማየሁ ደመቀ፣ እዩኤል መሐሪ እና ድምፃዊ ጌታቸው አስፋው ዳኝነት እየሰጡበት ቆይተውም ነበር።

በመጨረሻም አራት ምርጥ ድምፃዊያን ግንቦት 17/2016 አመሻሽ ከኢትዮ ለዛ ባንድ ጋር ታላላቅ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ፣ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች በተገኙበት ውድድሩን አወዳድሯል፡፡ ለፍፃሜ የደረሱ ድምፃዊያን ትንቢተ ኢሳያስ ፣ ዮሐንስ እሸቱ ፣ ብስራት አለማየሁ ፣ ራሄል ተሬሳ ሁሉም የየራሳቸው ሙዚቃ ሶስት ሶስት አቅርበዋል፡፡

በዚህ መሰረት የእለቱ አሸነናፊ የሆነው ድምፃዊ ዮሐንስ እሸቱ በምዕራፍ ሶስት በአሸናፊነት አጠናቋል፡፡

– ምርጥ አምስተኛ ደረጃ ሆኖ ያጠናቀቀው ኤፍሬም አበበ የሀምሳ ሺህ ብር ተሸላሚ፡፡

-በአራተኛ ደረጃ ብስራት አለማየሁ የአንድ መቶ ሺህ ብር አሸናፊ፡፡

-በሶስተኛ ደረጃ ትንቢተ ኢሳያስ የሁሉት መቶሺህ ብር አሸናፊ ፡፡

– ሁሉተኛ ደረጃ ራሄል ተሬሳ የሶስት መቶ ሺህ ብር አሸናፊ በተጨማሪም የግጥም እና ዜማ ደራሲ ሞገስ ተካ የግጥም ዜማ ስራ እንደሚሰጣት ቃልም ተገብቶላታል፡፡

– አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ዮሐንስ እሸቱ የአራት መቶ ሺህ ብር አሸናፊ ሆኗል፡፡

NBC ታለንት ሾው
ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
@yenevibe @biggrs
137560cookie-checkNbc ኢትዮጲያ የባለ ተስዖጦ የድምፃዊያንን ውድድር ፍፃሜውን አጊኝቷል፡፡ሶስተኛ ምዕራፍ የNBC ኢትዮጵያ የ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE