የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ሰኔ ወር 2016 ዓ/ም ወደ ሁለት የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎች በረራ ይጀምራል።
አየር መንገዱ ከሰኔ 10 ጀምሮ ወደ ወለጋ ፣ ነቀምቴ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል።
በረራው በሳምንት 4 ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ከዚህም ባለፈ ፥ በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ወደ አክሱም የሚደረገው በረራ ከሰኔ 1 ጀምሮ ዳግም እንደሚጀምር ታውቋል።
የአክሱም ሃፀይ ዮውሃንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፍያ በጦርነቱ በደረሰበት የከፋ ወድመት ምክንያት ከበረራ አገልግሎት ውጪ ሆኖ መቆየቱ ይታወሳል።
ከሰኔ 1 ጀምሮ ግን የመንገደኞች በረራ ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።