የጀኔቭ መኪና መሸጫ ድርጅት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት መፍትሔ እንዲሰጠው ጠየቀ።በ…

Reading Time: 2 minutes
የጀኔቭ መኪና መሸጫ ድርጅት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት መፍትሔ እንዲሰጠው ጠየቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በተለምዶ ደንበል አከባቢ የሚገኘው  ጄኔቭ መኪና አስመጪ ድርጅት ይዞታ የሆነው፣ ባለ አራት ኮከብ ሆቴል እንዲገነባበት ኤም.ኬ. ኤ.ኤስ ኃ/የተ/የግል/ ማህበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት አስተዳደር በማይፈቅደው መልኩና ህጉ ተላልፎ ሊሰጥብን ስለሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠየቁ።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የመንግሥት ቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 “ለልማት የማይፈለግ” በመሆኑ ኤም.ኬ. ኤ.ኤስ ኃ/የተ/የግል/ ማህበር  ለተሰኘው ድርጅት ሆቴል እንዲገነባበትና እንዲሰጠው የተላለፈውን ውሳኔ የከንቲባ መስተዳድሩ በማያውቀው መልኩና የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች ጋር በድብቅ በተሰራው አሻጥር መሰረት ከ1 ሺ ካሬ ሜትር በላይ መሬታችንን ተላልፎ እንዲሰጥ ውሳኔ ተላልፎብናል ሲሉ የጀኔቭ መኪና መሸጫ ድርጅት ስራ አስኪያጅ  አቶ እስራኤል ጌታቸው ተናግረዋል።

አቶ እስራኤል ጌታቸው እንዳሉት የመሬት ነክ ጉዳዮች ውሳኔ የሚያሳልፉ አካላት በማያውቁት መልኩ የቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3  ፅ/ ቤት ለኤም.ኬ. ኤ.ኤስ ኃ/የተ/የግል/ ማህበር  ተላልፎ ውሳኔ እንዲሰጠውና ሆቴል እንዲገነባበት አሳልፍያለሁ ማለቱን ከህግ አግባብ ውጭ በመሆኑ ጉዳያችን ክብርት  ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዲያውቁልን እንፈልጋለን ብለዋል።

ኮርፖሬሽኑ ቦታውን ለኮሪደር ልማት የማልፈልገው (የማይፈለግ) በመሆኑ ለተጠቀሰው ኤም.ኬ. ኤ.ኤስ ኃ/የተ/የግል/ ማህበር ተላልፎ እንዲሰጥ ያሳለፈውን ውሳኔ የከተማ መስተዳድሩ የመሬት ልማት አስተዳደር በማይፈቅደውና በአዲሱ መመርያ ያልተደነገገ ህግ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የሚመለከተው የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች እየደረሰብን ያለውን በደል እንዲያውቁልን እንሻለን ሲሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ለመገናኛ ብዙሐን በሰጡት መግለጫ ላይ  ተናግረዋል።

የመንግሥት የቤቶች ኮርፖሬሽን ቅርንጫፍ 3 ፅ/ቤት የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ ፅ/ቤት አአከፅ /03/30.1 ቁጥር  2013 ዓ/ም ጠቅሶ የፃፈው ደብዳቤ የከተማ መስተዳድሩ የመሬት ልማት አስተዳደር የሚመራበትን መመርያ የሚጥስ በመሆኑና የኮሪደር ልማት ስራ ባልተጀመረበት ጊዜ ቁጥርና አመተ ምህረት ጠቅሶ የፃፈው ደብዳቤ መርህ የጣሰ ደብዳቤ መሆኑን ክብርት ከንቲባዋ እንዲረዱት ሲል ድርጅቱ ቅሬታውን ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከንቲባ ፅህፈት ቤት የቤቶች ኮርፖሬሽን ፅ/ቤት ቅርንጫፍ 3 ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 18ና 17 በተለምዶ ደንበል ተብሎ የሚጠራው አከባቢ ያለውን ቦታችን እየተወሰደብን መሆኑን ተረድቶ እየደረሰብን ያለው ችግር ተገንዝቦ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጠን እንጠይቃለን ሲሉ የጀኔቭ መኪና አስመጪ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ እስራኤል ጌታቸው ተናግረዋል።

ችግሮቻችን ለተለያዩ መገናኛ ብዙሐን እንዲያውቁልንና ለሚመለከተው የመንግስት አካል በተለይም ለከተማ መስተዳድሩ እንዲያሳውቁልን ብንጠይቅም በኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ 3 የስራ ኃላፊዎች መረጃው እንዳይወጣ ጫና መፍጠራቸውን ተረድተናል ብለዋል።

በዚህ መሰረት የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር ክብርት  ከንቲባ አዳነች አቤቤ የደረሰብን ያለውን ችግር እንዲያውቁት ስንል ቅሬታችንን እናቀርባለን ሲሉ ገልፀዋል።
137380cookie-checkየጀኔቭ መኪና መሸጫ ድርጅት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት መፍትሔ እንዲሰጠው ጠየቀ።በ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE