ኋይት ሃውስ አዲስ ሆቴል በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አካባቢ ከሀያት ሆ…

Reading Time: < 1 minute
*
ኋይት ሃውስ አዲስ ሆቴል በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አካባቢ ከሀያት ሆስፒታል ጀርባ የተገነባው ኋይት ሃውስ አዲስ ሆቴል ትናንት ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ኋይት ሃውስ አዲስ ሆቴል ዘመናዊና ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በጠየቁ ግብአቶች የተደራጀ እና የተሟላ አገልግሎትን የሚሰጡ 30 የምኝታ ክፍሎች ፤ የስብሰባ አዳራሾች፣ ባር እና ሬስቶራንት፣ ላውንጅ፣ ጅም ፣ስፖ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት መዘጋጀቱን የሆቴሉ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ወይዘሮ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሆቴሉ ለምግብ ግብዓት ከሆኑት መካከል የበሬ ስጋ ሆቴሉ በራሱ ከሚያደልባቸው ከብቶን በልዬ ጥንቃቄ በእንስሳት ሀኪም ተመርምረው እንደሚቀርቡ ወይዘሮ ፍሬህይወት ታምሩ የገለጹ ሲሆን ማኀበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት በኩል በየቀኑ አቅም ለሌላቸው ወገኖች ማዕድ እንደሚያጋራ ገልጸዋል።

ካለፈው ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም በሚቆየው ልዮ የምረቃ መርሃግብር ላይ በየቀኑ ከ500 ያላነሱ እንግዶችን ተቀብሎ እያስተናገደ ይገኛል ያሉት የሆቴሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሄኖክ ብርሃኑ ከ45 ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚ እና ከ127 በላይ ለሚሆኑ ደግሞ ጊዚያዊ የስራ እድል እንደፈጠረ ተናግረዋል።
135460cookie-checkኋይት ሃውስ አዲስ ሆቴል በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አካባቢ ከሀያት ሆ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE