"በፍቅር መዝገብ ላይ ቀድሞ ቢፅፈንም
አንድ ሁኑ ብሎናል ማንም አይለየንም
ታድያ ምን አስፈራን ትህዛዙን ሰው ላይሽር
ከ ላይ ከተሰጠን የማይናድ ፍቅር"…
ድምፃዊ የዜማ እና ግጥም ደራሲ ድምፃዊ አርቲስት ታምራት ደስታ ከ ሐዋሳ እስከ አዲስ አበባ ግንቦት 25/1971 ዓ.ም የፍቅር ከተማ ከሆነችሁ አዋሳ ልዩ ስሙ ጥቁር ውሀ የተሰኘ ቦታ ተወለደ ፡፡
ተወዳጁ ድምፃዊ ታምራት ደስታ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በ ሀዋሳ ታቦር ት/ቤት እንዲሁም በካቶሊክ ሚሽን ት/ቤት የተከታተለው የሁለተኛ ደረጃ ደሞ ትምህርቱን በሻሸመኔ በመጓዝ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርቱን ተከታትሏል ተከታትሏል፡፡
ገና ለጋ እያለ በሙዚቃ ፍቅር ይነደፋል ሙዚቃ ይሰማል አብሮም ያቀነቅን ነበር ይንን የሙዚቃ ፍቅር እውን ለማድረግ ወደ ድሬዳዋ በማቅናት በኮተኒ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የሙዚቃ ቡድን ጋር በመቀላቀለ በዛም ሳለ ችሎታው እጅግ ያስገርም ነበር በኮተኒም ጨርቃጨርቅ 150 ብር እየተከፈለው ስራ ጀመረ ፡፡
በኃላም በሙዚቃ ጉሮሮውን ካሟሸ በኃላ በ 1990 ዎቹ መግቢያ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በተለያዩ የምሽት ክበቦች ሰፊ ጊዜውን በመሰራት ሀዋሳ የነበረውን ችሎታ እጅግ አበልፅጎት በአዱ ገነት ምሽቶች ተወዳጅነትን አተረፈ።
እንዲህ እንዲያ እያለ ወደ ራስ ማወቅ እራስ ማሳየት ቦታ ሲደርስ በስሙ የሰየመውን ''ታሜ'' የተሰኘ አልበም በማራቶን ሙዚቃ ቤት ያተመውን ብዙም አድማጭ ዘንድ ጆሮ ያልገባውን አደረሰን በመቀጠል በ 1994 አ.ም ሀኪሜ ነሽ ሲል እንደ ገና ሪአሬንጅ በማድረግ አደረሰን በ1996 አ.ም አንለያይም ከ ዳግማዊ አሊ ጋር ሰሩ በ2000 ተወዳጅነትን አትርፎ '' ካንቺ አይበልጥም'' ሲል በ2006 አዲስ አልበም አበረከተ 2006 ''ከዛ ሰፈር "የተሰኙ አልበሞችን አደረሰን ፡፡
ድምፃዊዊ ታምራት ደስታ ለሰው ተራፊ ነበር ተወዳጅ ሙዚቃዎችን አሻግራል ለ ገረመው አሰፋ ፣ ለወንድሙ ጅራ ፣ ለጥበቡ ወርቅዬ፣ ይርዳው ጤና ፣ታደለ ገመቹ ፣ሄለን በርሄ ግጥም እና ዜማ በመስጠት አይተኬ ሚናውን ተወቷል ፡፡
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
ግጥም ዜማ ስራ አብሮ ከሰራቸው መሀከል ጌትሽ ማሞ ፣ አብታሙ ቦታለ ፣ ኃይለእየሱስ እሸቱ እና የመሳሰሉት በቅንብሩ ኤልያስ መልካ ፣ ዳግማዊ አሊ ፣ ሚካኤል ሀይሉ ባወጣቸው አልበም ውስጥ ተሳትፎ ነበራቸው ፡፡
ሚያዚያ 10 /2010 አም ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል ፡፡
የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት ስለ ሰጠከን ሙዚቃ እጅግ ከልብ እናመሰግናለን ፡፡
@biggrs @yenevibe
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ