"
በበራው በጠፋው በጭንቀት አትግፋው
እንዲህ ነው ሂደቱ የቀን የለሊቱ ፡፡"
ተጓዝ እንጂ በተስፋ
አንገትህን አትድፋ" …የሙዚቃ ክብሯ የተገለጠበት ቤተሰባዊነት እና አብሮነት ሚስጥር ፋና ላምሮት…
ፋና ላምሮት የአራተኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ እንደ ወትሮ ሁሉ ድምቀቱን ይዞ ተጠናቋል በልዪ ስነስርዓት አስገራሚ ፣ አስደማሚ ፣የሙዚቃ ከፍታ ፣ ሙያዊ ስነምግባር ፣ ቤተሰባዊት ትስስር የተመለከትንበት ነበር ፡፡
*
ምን አዲስ ነገር አለ…
- በዝግጅቱም ታላላቅ የኪነጥበብ ሰዎች በኢትዮጲያ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ጉልህ አበርክቶ ያላቸው በዚህ አመት በሕይወት ላጣናቸው ለ ሂሩት በቀለ ፣ ጌታቸው ካሳ ፣ ሙሉቀን መለሰ ፣ እናኑ ደጉ ፣ እስራኤል መስፍን ፣ ሳባ ይሁነኝ የክብር ምስጋና አቅረበዋል ፡፡
- አዲስ እና ወጥ ሙዚቃ የተሰጣቻውን "ቀና እንድትል" የተሰኘ ስራ አቅርበዋል ግጥም እና ዜማ አቡዲ ቅንብሩን ታምሩ አማረ ሲሆን ተወዳዳሪዎች ከ ዛይን ባንድ ጋር አቅርበዋል ፡፡
- የእለቱ የክብር እንግዳ ድምፃዊት አመልማል አባተ እና የግጥም ዜማ ደራሲ ጋሽ ፀጋዬ ደቦጭ ናቸው በእለቱ ድምፃዊት አመልማል ለተወዳዳሪዎች ብርታት እና ነጥብ ሰታለች ጋሽ ፀጋዬ ደቦጭ በመድረኩ ሐሳብ ሰቶ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ስራ አስፈፃዊ አቶ አድማሱ ዳምጠው እጅ የ200 መቶ ሺህ ብር ተበርክቶላታል ፡፡
- ተወዳዳሪ ሄኖክ ብርሀኑ የጥላሁንን ገሰሰን ዘፈን አለፍኩሁሉን ችዬ የተሰኘው ሙዚቃ( በሻዶ አርት) shado Art በመጠቀም አቅርበዋል አርቱን ያቀረቡት ፀጋዬ እና ጓደኞቹ በጋራ በመሆን ነው ፡፡
- ውድድሩ ሲካሄድ የቀድሞ አሸናፊዎች በቦታው በመታደም ዝጅቱን ተከታትለዋል አሉላ ገብረ አምላክ ፣ ያለምወርቅ ጀምበሩ ፣ ኤልያስ ተክለ አይማኖት እና ዳንኤል አዱኛ መተዋል ፡፡
- የፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው መልዕክት'' ፋና ላምሮት እራስን ማበልፀግያ የነፍል ምግብ ነው" በተጨማሪም ባለሞያተኞችን ማሰባሰብ እና ምስጋን ማቅረብ ማገዝ ይኖርብናል ብለዋል ፡፡
-ከግጥም እና ዜማ ከ ቅንብር አንፃር ስንመለከት ጋሽ ተስፋዬ ለማ ፣ አለምፀሐይ ወዳጆ ፣ አቡዲ ፣ አበጋዝ ፣ ሙላቱ አስታጥቄ ፣ የታምሩ አማረ እና የመሳሰሉት ቀርበዋል
*
ዳኞች ከልስትም ከስሜትም ለተወዳዳሪዎች አስተያየት ሰጥተዋል…
የተወዳዳሪዎች ለውጥ ፣ የሙዚቃ መግቢያዎችንማድነቅ ፣ ስሜት ፣ ውበት ፣ ኪ መረጣ ፣ ተዝናኖት ፣ ቅኝት ፣ ቴክኒክ በብልጠት መጠቀም ፣ ቃላቶን በጥራት ማቀበል(ዲክሽን) ፣ ቫልዩ አድ( አዲስ ነገር መጨመር ) ፣ ሜሎዲ ከርቭ ( የዜማ እጥፍት) ፣ ፎክ(ባህላዊ አቀራረብ) ፣ የጥምረት ፣ ናዛል ቮይስ( ወደ አፍንጫ የሚመጣ ድምፅ)፣ በራስ ድምፅ ማቅረብ የመሳሰሉት ቀርበዋል ፡፡
-
ዛይን ባንድ ከተወዳዳሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ወደ 12 የሚጠጉ ሙዚቃዎች አቅርበዋል ፡፡
ጥላሁን ገሰሰ(የኔ ፍላጎቴ) ፣ ሙሉቀን መለሰ (ውቢቲ) ድጋሚ የተጫወተው ወንድሙ ጅራ ነው ፣ አመልማል አባተ(ተሸነፍኩላችሁ) ፣ የፀሐዬ ዮሐንስ( ደመረች) ፣ ማሪቱ ለገሰ ( አንባሰል) ፣ እሳቱ ተሰማ ( ድማማ) ድጋሚ የተጫወተው ዳዊት ፅጌ ፣ ኤፍሬም ታምሩ ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ( ደሞ ደሞ) ፡፡
*
ተጋባዥ ዳኞች እና መደበኛ ዳኞች የሕይወታችን ስንቅ ለተወዳዳሪዎች ብርታት ለተዋል ፡፡
-
ብሩክ አሰፋ ፡ ዋናውን ሙዚቃ ሳይጎዳው ግጥም ጭሮ ማቅረብ ስሜቱን አስማምቶ ያስኬዳል ፡፡
- የሰው ልጅ ይለያል በሙዚቃ ሂደት ውስጥ ምክንያቱም ቃልን እና ዜማን አዋዶ ስለ ሚዘፍን ነው ፡፡
- አቤል ሙሉጌታ ፡ ዝና ጤናን ይመስላል ተንከባከቡት በመንከባከብ ውስጥ ዝናንም ጤናንም እንጠብቃለን ፡፡
- ሙዚቃ መኖርን ይጠይቃል
-
ብሌን ዮሴፍ ፡ ሙዚቃን በማወቅ ውስጥ ስንጓዝ ብዙ እናተርፋለን ::
- ቀና እንድትል የተሰኘን ስራ ሁላችሁ አራታችሁም ብታቀርቡት እናላለሁ ስሜቱ ፣ ውበቱ፣ እጅግ ይገርማል ፡፡
-
ተጋባዥ ዳኞ አመልማል አባተ ፡ ፍቅር እና ጊዜ የተሰጠው ልጅ ከምንም ይበልጣል በጠቀሙበት ፡፡
- አንድ ሰው ተምሮ ዶክተር ሊሆን ይችላል ኢንጅነር ሊሆን ይችላል ግን ድምፃዊ መሆን አይችልም ምክንያቱም ድምፃዊነት የተፈጥሮ ስጦታ ነው ፡፡
- ተጋባዥ
ጋሽ ፀጋዬ ደቦጭ - ያቀረባችሁት ሙዚቃ እንደ መልካችሁ ተመሳሳይ ነው ስሜቱ ፣ ውበቱ ይገርማል በርቱ ፡፡
- ፋና ስንል ወጋገን ነው ፍና ማለት ብርሀን ነው አመሰግናለሁ ፡፡
*
ተወዳዳሪዎች ለፍፃሜ ባደረጉት ትንቅንቅ አሸናፍዎች ተይተዋል ፡፡- በአምላክ ቢያድግልኝ - የአንድ ነጥብ አምስት ሚልየን (1.500000) ብር እና የክብር ዋንጫ አሸናፊ በመሆን ፡፡
-ሐብታሙ ይሄነው -የአንድ ሚልየን ብር (1,000000) አሸናፊ በመሆን ፡፡
-ሄኖክ ብርሀኑ የምስት መቶ ሺህ ብር(500,000) አሸናፊ በመሆን
- ትዕግስት አስማረ የሶስት መቶ ሺህ ብር አሸናፊ(300,000) አሸናፊ በመሆን እና ቀና እንድትል የተሰኘ አዲስ እና ወጥ ሙዚቃ የግልዋ አድርጋለች ፡፡
በመስተ መጨረሻ የዚህ አስተዋፅፆ ላበረከቱት የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል ፡፡
ፋና ላምሮት
ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
( በምዕራፎቹ እንገናኝ) በዚሁ በተፈፀመ
አሳብ አስተያየት
@temela አድርሱኝ
@biggrs @yenevibe