«ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ እንሁን» በሚል የግንዛቤ ማስጨባ ተካሄደ።ትኩረት ለሴቶችና ለህፃናት ማህበር “ድምፅ…

Reading Time: < 1 minute
«ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ እንሁን» በሚል የግንዛቤ ማስጨባ ተካሄደ።

ትኩረት ለሴቶችና ለህፃናት ማህበር "ድምፅ ለሌላቸው ድምጽ እንሁን" በሚል ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው የማዕከሉ ግራር የሕጻናት መንደር ለተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር በዛሬው "እለት አደረገ።

ትኩረት ለሴቶችና ለህፃናት ማህበር ራዕይን በማስፋትና በሀገራችን በአይነቱ ለየት ያለውን ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸውን ህፃናት መንደር ከመንግስት በተሰጠው 2632.86 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነውን ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸውን ህፃናት መንደርን ግንባታ አጠናቋል፡፡

በቀጣይም በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው ህፃናት እና እናቶቻቸውን ተደራሽ ለማድረግ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል መንታ G+9 ፎቅ ለመስራት አቅዷል፡፡ ይህንንም እቅዱን ለማሳካት ትኩረት ለሴቶች እና ለህፃናት ማህበር ሲሆን ዋና አላማውም ተደራራቢ የጤና ችግር ስላለባቸው ህፃናት እና እናቶቻቸው በማህበረሰቡ ውስጥ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ ተገልጿል።

ከተመሰረተ 17 ዓመታትን ያስቆጠረው ትኩረት ለሴቶችና ለህፃናት ማህበር በእነዚህ ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎች ለችግር የተጋለጡ ሕፃናትን፣ በድህነት የሚኖሩ ሴቶችን እና የተለያዩ ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዲሁም የኤችአይቪ ኤድስን ስርጭትን ለመቀነስ የተለያዩ የልማት ፕሮግራሞችን ነድፎ በአጠቃላይ 12,000 ሺህ የሚደርሱ የህብረተሰብ አካላትን ሲደግፍ እንደቆየ በመግለጫው ተነግሯል።

በአሁኑ ወቅት በድርጅቱ ውስጥ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው 18 ህጻናት የሚገኙ ሲሆን እነዚህን ህጻናት በጤና ፤ በምግብ፣ በመጠለያ፣ በትምህርት እና በስነ-ልቦና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
119880cookie-check«ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ እንሁን» በሚል የግንዛቤ ማስጨባ ተካሄደ።ትኩረት ለሴቶችና ለህፃናት ማህበር “ድምፅ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE