Search
Search

ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 75.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

Share Post ►

ኢትዮ ቴሌኮም በ2015ዓ.ም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 75.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት በስካይ ላይት ሆቴል ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ለመጡ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ አስታወቁ።

የተቋሙ የዘንድሮ ገቢ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 23.5 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ገቢውን በ25 በመቶ ለማሳደግ አቅዶ የነበረ ሲሆን ከእቅዱ 101 በመቶ ማሳካቱን ተገልጿል። ይህ ገቢ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ23.5 በመቶ ብልጫ አለው ያሉት ወይዘሮ ፍሬህይወት ታምሩ የተገኘው ገቢ በአገልግሎት አይነት ሲታይ የድምጽ አገልግሎት 43.7 በመቶ ድርሻ ሲኖረው ዳታና ኢንተርኔት 26.6 በመቶ ፣ ዓለም አቀፍ ገቢ 5 በመቶ እሴት የሚጨምሩ አገልግሎቶች 6.9 በመቶ ፣ የቴሌኮም መጠቀሚያ መሣሪያዎች ሽያጭ 4.7 በመቶ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች 7.2 በመቶ ድርሻ አላቸው፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ተጠቃሚ ደንበኞች ብዛት 72 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን አፈፃፀሙ ካለፈው በጀት ማጠናቀቂያ ከነበረበት ጋር ሲነጻጸር የ8 በመቶ እድገት፣ እንዲሁም ከእቅድ አንጻር የ98 በመቶ አፈጻጸም ተመዝግቧል፡፡

በአገልግሎት አይነት ሲታይ የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት 69.5 ሚሊዮን፣ የመደበኛ ብሮድባንድ 618,3 ሺህ የመደበኛ ስልክ ደንበኞች 853.6 ሺህ እንዲሁም የዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 33.9 ሚሊዮን ናቸው፡፡ የቴሌኮም ስርጸት መጠን 66.8 በመቶ ሆኗል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም ላይ ካሉ 774 ኦፕሬተሮች መካከል በሞባይል ደንበኛ ቁጥር በአፍሪካ 2ኛ ደረጃ የያዘ ሲሆን በዓለም 21ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ከ300 በላይ ከተሞች የ4ጂ ኔትወትርክ ያቀረበው ኢትዮ ቴሌኮም ትርፋማ መሆኑን አስመልክቶ ለደንበኞቹ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የድምጽ ፣የኢንተርኔት እና የኤስኤም ኤስ ስጦታዎችን አበርክቷል።

(ጌች ሐበሻ)
ፎቶ Abinet Tamirat

Share Post ►

Trending Today

You may also like

Leave a Comment

* By using this form you agree you are responsible for what you comment.

1 comment

moges July 18, 2023 - 11:22 am

በርቱ አንደኞች

Reply