Search
Search

ተንቀሳቃሽ ቅርሳችን የዜማየግጥም ደራሲ የጊታር እና ክራር ሙዚቃ መሳርያ ተጫዋች እንዲሁም ፕሮዲውሰር  ታላቁ ይልማ ገብረ አብ ዛሬ ልደቱ ነው

Share Post ►

ልደቱን በማስመልከት 2000ሺህ በላይ ስራዎች መሀል አንዱን መዘዝ አርገን ለማየት ወደድን …

የይልማ የአገጣጠም ብስለት ፣ በሚገባው ልክ መስጠት ይልማ ተክኖበታል እዚህ ሙዚቃ ላይ ይህንን መስካሪ ነው ፡፡

በነገራችን ላይ አብዛኛውን ግጥም ለ ኤፍሬም ታምሩ ሰቶታል ወደ 76  ያህል ሰቶታል በቀዳሚነት ለ ድምፃዊ  አረጋኘኝ ወራሽ 90ያህል ግጥም ለመጀመርያ ጊዜ የሙዚቃ ግጥም ሐ ብሎ የሰጠው የጀመረው ለድምፃዊ ለሙሉቀን መለሰ ራሱ ላይ የደረሰው እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ”የዓይኔ ነገርማ” ከዛም 40 ያህሎችን ሰቶሰቶል።

(#ይልምሽ#በኤፍሬም#ጎሮሮ#ከናገራቸው#መሀል#ቢልልኝ)

ቢልልኝ :- ሐሳብ ቢሳካልኝ ፣ ውጥኔ ቢሳካ ፣ ያለምኩት እውን አልሆን አለኝ እንደ ሰው ቢሆንልኝ ምን አለ እያለ በተብሰለሰ አንጀት  በጥያቄ ውስጥ እየኖረ  ሐዘኑን የሚወጣበት ሙዚቃ ነው አሳዝኖ ጀምሮ አሳዝኖ የሚያልቅ ስሜትን ያዢ ነው ፡፡

ቢልልኝ ቢልልኝ እንደ ሰው ቢልልኝ
ምን አለ ቢልልኝ አንቺ ቢጥልልኝ …

ሀገሩን ብዞር ባስሰው በእኔ ልክ እንደ  አንቺ አይነት ውብ የለም በሐሳብም ፣ በቁንጅናም ፣ በመረዳትም ሁሉ ነገር ጓዳዬን አዋቂነሽ ብዙ ሰው ካንቺ ውጪ አይቼ ግን እንደ አንቺ የለም ፡፡

አንቺ ልጅ ጭንቄን ምነው ብረጂው ?
ሰላም ገላዬን በናፍቆት ባትጎጂው
ትዝታሽ ሆዴን በሐሳብ እያረሰ
መውደድሽን ውስጤን እያርመሰመሰው…

መላ ፈላጊ በዞር ቢያጤን መልስ ቢሻም መድሐኒቱ አንድ እና አንድ የሆነበት መልስ ተደምሮ ሌላው በጫንቃው ናፍቆት እና ትዝታ ያሰቃየዋል ይልማም  በሩን ዘግቶ በጥሞና ስላለፈው ታሪክ እያሰበ በእንባ የገጠመው ይመስላል ልክም ”የዓይኔ” መች ትረሳና ለሷ ያለው ፍቅር  ትልቅ ነው ኤፍሬምም ያንን ስሜት በመረዋ ድምፁ እየነገረን ነው ፡፡

አንጄቴን አንጄቴን በልቶ እጨረሰው
አታዝኝም ወይ ለተሸነፈ ሰው …

ምንም ላይ ጎበዝ ብትሆን ፣ ዓለም ላይ ስኬት ሁሉ ብታይ” ነጥብ አስጣይ” የሆነ ነገር ማጋጠሙ አይቀሬ ነው ፍቅር የሚባል ማህበል አለ ፡፡

ዛሬ ብረታ አትጨክኝ በእኔ
ሐሳቤ ነበርሽ እንዳንቺው ለጎኔ
ጥሎብኝ ጥሎብኝ ባትሆኝ ሰቀቀኔ
አይ ወድጄሽ በጎዶሎ ቀኔ …

ስለ ሁሉም ተማርከህ ሳትገድድ እጅ የምትሰጠው ነገር ቢኖር ፍቅር ነው ፡፡ የማይንገዳደግ ገንዘብ ቢለጥህ ቅንጡ ቦታዎች ደርሰህ ብትመጣ ይንን ሁሉ አያሸንፈውም እውነተኛ ስለሆነ ፡፡

አንድ ቀን አንድ ቀን አገኝሻለሁኝ
እህህ እያልኩኝ እኖረዋለሁኝ”

አንድ ቀን ውድ ስጦታ መች እንደምትፈታ የማትታወቅ ግና በተስፋ በናፍቆት ታሽጋ የምትጠበቅ ናት ፡፡

በእጅ የያዙት ወርቅ እንደ መዳብ ይቅጠራት በእጅህ ሳለች ያለመዘናጋት ፍቅርን መጠበቅ አለዛ እንደ እግር እያሳት እያብከነከነ ያኖራል ፡፡

አይቀርም አይቀርም ይሳካልኝ እያልኩኝ
አንድ ቀን አንድ ቀን ይሆናል እያልኩኝ
አይ በተስፋ እጠብቃለሁኝ…

ይልማ ገብረአብ በድንቅ ግጥም ከተበው ዜማውን ፍሰት በአበበ ብርሀኔ ተከወነ ቅንብሩን ተወዳጁ አቀናባሪ ቴዲ ማክ /ቴዎድሮስ መኮንን / ዘመን እንዳይለዋውጥ አርጎ ሰራው ፡፡

ይልማ ገብረ አብ ዛሬ ልደቱ ነው እንኳን ተወለድክ አንተ ባትኖር ማን ይሰጠን ነበር እንዲህ አይነት ሙዚቃ፡፡

የሞያ ጎደኞቹ ፣ ድምፃዊያን ፣  አንድ ቀን ለታላቅ አበርክቶህ መድረኮች ይዘጋጃሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡

ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

Share Post ►

Trending Today

You may also like

Leave a Comment

* By using this form you agree you are responsible for what you comment.